በአለም ስራ ኣእምሮዬ ተሰውሮ ፤
በስጋ እምነት ልቤ ሰክሮ፤
በስጋ እምነት ልቤ ሰክሮ፤
ድረሽልኝ ድንግል ማርያም ፤
ያለ እርድታሽ ተስፋ የለም። (2)
ያለ እርድታሽ ተስፋ የለም። (2)
በቀላሉ ተስፋ አጣለሁ ፤
ከመጀመር ሳልበረታ እደክማለሁ፤
ከመጀመር ሳልበረታ እደክማለሁ፤
ድረሽልኝ ድንግል ማርያም ፤
ያለ እርድታሽ ተስፋ የለም። (2)
ያለ እርድታሽ ተስፋ የለም። (2)
ሲቸግረኝ የምለምን ማማለድሽን ፤
የደላኝ ቀን የምረሳው ውለታሽን፤
የደላኝ ቀን የምረሳው ውለታሽን፤
ድረሽልኝ ድንግል ማርያም ፤
ያለ እርድታሽ ተስፋ የለም (2)
ያለ እርድታሽ ተስፋ የለም (2)
ደንግል ማርያም የአምላክ እናት ፤
የአለም ተስፋ የአማኝ ኩራት ፤
የአለም ተስፋ የአማኝ ኩራት ፤
አፌ ስምሽን ይጠራ ዘንድ
እኔ ማነኝ ?
ፈውስ እሻለሁ፤
ከአለም ስህተት ደጅሽ ጥሪኝ፤
እድናለሁ።
እኔ ማነኝ ?
ፈውስ እሻለሁ፤
ከአለም ስህተት ደጅሽ ጥሪኝ፤
እድናለሁ።
ደረሽልኝ ቅደስት ሆይ የዓለም ተስፋ
በሃጥያቴ እንደሰከርሁ እንዳልጠፋ ።
በሃጥያቴ እንደሰከርሁ እንዳልጠፋ ።
እሱባለው ቸኮል