አምና በዚህ ጊዜ ፤
ኮሮና ሳይመጣ መተቃቀፍ ሳለ
ከቤትሽ ከወንዜ፤
ፍቅራችን ሳይሻክር አዲስ ከነበረ
አይኔን ጨፍኜልሽ በኮረብታዉ መንገድ ትመሪኝ ነበረ ።
እንዳትነካኩ ተራራቁ ተብሎ
አዋጅ ሳይነገር፤
አምና በዚህ ጊዜ በፍቅር ትኩሳት
ተቀጣጥለን ነበር፤
ተቃቅፎ መሳሳም ለሞት ይጋብዛል ፤
ተራርቀው ካልኖሩ በሽታ ይይዛል ፤
አፋችሁ ይሸፍን ይጨፈን ሳይባል፤
አምና በዚህ ጊዜ ዉጪያችን አደለም
ዉስጣችን ተገልጧል።
ትዝ ይልሽ ከሆነ እንደኔ ከታየሽ
ጨለማ ሲመጣ እናትሽ ሲተኙ
በሞስኮት ሽዉደሽ፤
ስትመጪ ወደኔ መነካካት አድጎ
ተቃቅፈን ስናመሽ፤
ፍቅራችን ግለቱ ሳይበርድ ሳይታገስ፤
ተራራቁ ተብሎ መሳሳም ሲከሰስ ፤
የአምናው ትዝ እያለኝ የፍቅርሽ አሻራ
ከልቤ ባይጠፋም፤
ከሮናን በማለት እርቀት ስለጠበቅሽ
ከጎኔ የለሽም።
መነካካት ድርግም ፤
መተቃቀፍ እልም፤
መሳሳምም የለም፤
እሱባለው ቸኮል