ያመነውን ከድቶ ደልቶት ያልተቀጣ
አሁን እናያለን፤ አደራውን በልቶ ፍትህን ያሳጣ
ከጎናችን አለን፤ ሰርቆ የከበረ የደላው ሲበዛ
ሰው ጤፉ የሆነ ይሉኝታውን ሸጦ
ንብረቱን የገዛ ግሩም ፍጥረት በዝቷል እሱን እናውቃለን ፤ ምን አማራጭ አለን?
አቤቱ ጌታችን ማረን እንላለን ፤
የመሬትን ንቀን የሰማይን ተስፋ እንጠብቃለን ።

እሱባለው ቸኮል / ህዳር 2014