በአራት እግሩ ሲሔድ ሲቆም በሁለቱ
ሲያጌጥ ሲለባብስ የሰው ልጅ ኩራቱ።
ይኖር ይመስለዋል ዓለም እንዲህ ጣፍጣ
መድከም መንገዳገድ እርጅና ሳይመጣ።
ወዙ ሲያብለጩለጭ ፈገግታው ሲያበራ
"ሰው እኔ ነኝ እኮ ማን አለ ጠንካራ"
ብሎ ሲደነፋ ቆሞ ሲንጠራራ።:
ፍፁም አያስብም ሰዓቱ ሲቆጥር
ነገ ዛሬ ሆኖ ወደትናንት ሲዞር:
ቀድሞ አይሰማውም ደቂቃው ማለፉ
ቀኑ መሸሽቶ ነግቶ ሲለፈልፍ ወፉ ።
ዛሬ እኮ ዛሬ ነው ነገም ቢሆን እሱ
ከአእድሜው ላይ አንድ ቀን ሁለት መቀነሱ ፡
"ይህ እርጅና አይደለም ዛሬ ጤናማ ነኝ"
"ተመልከት ጡንቻዬን ዝለል ብረር ሲለኝ"
ነገ ሃያ ዘጠኝ በዓመቱም ሠላሳ፣
"አበድክ ጤናም የለህ ገና ነኝ ጎልማሳ"
ሠላሳውም አልፎ አርባ ዓመት ሲሆነው
ቁጭ በል ተጫወት ይቅርብ ሩጫው።
"ማሞ መስታዎቱን እስቲ ወዲህ ስጠኝ"
"ከሸበቴ በቀር አሁንም ወጣት ነኝ"
አምሳም ሥድሳም አልፎ ዘጠና ቢሞላ
ሞኝ ነው የሰው ልጅ ማሙዬ ተላላ።
ፅድሜ እያሳቀቀው እርጅና ቤት ገብቶ
ዞር ብሎ ሲያስተውል ያንን ዳገት ወጥቶ
መርበትበት መደንገጥ ያኔ ነው ሐዘኑ
"ይገርማል ይደንቃል እንዴት ሔደ ቀኑ፣"'
ሁሉም አዲስ ነገር አይቶ የማያውቀው
ከቶ ምን ልብስ ነው ሳያውቅ ያጠለቀው፤
ወሀ ውስጥ ቆይቶ በሳት የተቆላ
ቆዳው ተጩማዶ ሲመስል ባቄላ፤
ጅማቱ ሲታሰር እግሩ መሔድ ሲተው
እጁ ሲንቀጠቀጥ መጩበጥ ሲያቅተው፤
ዓይኑ እየደከመ ጆሮው ሲያወላውል
አንሱኝ ብድግ አርጉኝ ያዙኝ እቀፉኝ ሲል፤
አእንዳያፍር ሲባል እንዳይወድቅ ሲጠገን
ሕልም እየሆነበት የበረረው ዘመን፤
ለፅድቅ ነው ብሎ ሞት መጥቶ ሲያነሳው
ሰው ያብዳል ይጮኻል ያለቅሳል በሬሳው፤
ካለመኖር መጥቶ አእአኖራለሁ ይላል
ሲሞትም በኋላ ቆይቶ፤ ይነሣል፤
መኖር የሚሜሉትን ይኸን ቃል ቢያገኘው
መንካትም መዳሰስ መጩበጥ ቢቻለው፤
እንደብር በኪሱ ወይ እንደቀለበት
እጣቱ ላይ አርጎ መኳተን ይብዛበት?
ማ መሆኑን ሳያውቅ ራሱን ሳይገምት
እንደጥንግ ለግተው ወደላይ የጣሉት፤
አየር ላይ ተንሳፎ የሚይዘው ሲያጣ
ባክኖ ተሽሸከርክሮ ዞሮበት ሲመጣ፤
በስስታምነት ራሱን ያኮራል
"እግዜርን አየሁት ልክ እኔን ይመስላል"
አሱ ለዚህ ዓለም ቅንጣት ኢምንት ነው
ይህ ዓለም ለዚያኛው ያኛው ለወዲያኛው
ተያይዞ ሲሔድ መጩረሻም የለው።
የአእምሮው መብራት እያነሰ ኃይሉ
እየረቀቀበት ሲጠፋበት ውሉ።
ጭጋግ እየሆነ ምሥጢሩ ሲሳነው
ካለመኖር ፈጥሮ መሬት ላይ የጣለው
አእንቆቅልሽሸ ሆኖ ዝም ብሎ የሚያየው።
ማነው፤ ምን ነው፤ የት ነው፤ አንዴት ነው ከማለት
ሲሔድ ያገኘዋል በቀጠሮው ሰዓት።
ሳር መሳይ ጎዝጉዞ ካሳለፈ እንቅልፉን
ባይለብስስ ባያጌጥ ቢሆን ራቁቱን ፡
ፀሐይ ስትገባ ካየ ስትወጣ
ወሀ ከወንዝ አፍሶ በፍኙ ከጠጣ።
ተገዢ ከሆነ ሥራውን ከሠራ
ሓሳቡን ሳያውቀው በሌላው ሲመራ።
አለ ብሎ ቆርጦ የለም ብሎ ካለ
በሁለቱም ቆሟል መንገድ መች ቀጠለ
እንጀራና ወጡን ደኅና አርጎ ከበላ
ሰው እኮ ከብት ነው አይ ሞፔ ተላላ።
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ