ያዘቀጠው አሰር እየደፈረሰ
የተቀጣጠለው አንጩቱ እየጩሰ
መሬት ቁና ሁና የሰው ልጅ ሲጩንቀው
እሳት ተያይዞ አገሩን ሲያለብሰው
ባለቤት ተሰዶ አዱኛ ፈራርሳ
አሞራ ሲያንዣብብ ተከምሮ ሬሣ
ሥጋ ሲርበደበድ ነፍስ ይሸቆጠቆጣል
የኔ እያቀዘፈው ደም ይገነፍላል፡
ኮሽ ባለ ቁጥር ዞሮ ሲገላመጥ
እየተንሻተተ ገደሉን ሲባጥጥ
ሲቃትት ሲደክም ሲርበው ሲጠማው
ሥጋውን በመካድ ሞትን ይመኛል ሰው።
የፍቅር ጥላነው ጭጋግ የደስታ
ኀዘን መንገላታት፤ መታሠር መቸገር
መቁሰል መሰቃየት የሌለው ፀጥታ
ያንድነት እከክ ነው ልብሱ የነተበ
በላብ በጭቅቅት ገላው የረጠበ
ተለዋዋጭ መልኩ ያልታወቀ ግቡ
አልቋል ሞቷል ሲሉት ያው ይነትራል ልቡ።
ሥጋ ተለያይቶ ሲቀር አጥንታቸው
ማንንም በስሙ መጥራት የማንችለው
መልካቸው ሲጠፋ ሁነው እንዳልነበር
እነሆ ርስታቸው የእኩል ቤት መቃብር።
መድፍ የተከላቸው መትረየስ ዘርዝሮ
ቦምብ የመገባቸው አይሮፕላን በሮ፣
ታንክ በደነጎረው ጠመንጃ ዘርቷቸው
ጢስ ወሀ እየሆነ ሲጠጡ ባፋቸው
የታል የበቀሉት ወዴት ነው ቦታቸው?
ልምላሜአቸው የታል ፍሬያቸው የታለ?
ሐውልቱ ድንጋዩ ምን አጎነቆለ!
ባንድ በኩል ደግሞ
የሰላም ሚዛን ነው፤
የበዛን አረሞ
የሚያስተካክለው።:
ሰላም ብዙ ሲቆይ ሥሩ ይሻግታል
መሠረቱ ዝጎ ቀስ ብሎ ይወድቃል፤
አንስቶ በመካብ የፈራረሰውን
ቀብሮ በመለሰን ሲያድስ መሠረቱን፤
ኃይለኛ ሲገባ ሲከተል ዓላማ
ባላህ እርጋ ብሎ አዋጁን ሲያሰማ፤
ይኸው ተጀመረ አዲስ ዓይነት ሰላም
ዳገመኛ እስቲወድቅ ፈርሶ እስቲደመደም፤
ሰላም ያቻት ብሎ ሁሉም የሚጮኸው
ክፉ ቀን አታምጣ ብለን የምንተቸው፤
በፀሎታችን ውስጥ መሪ እንዳያሳጣን
ወድቀን እንዳንቀር ተገዥ በመሆን፤
ያቻት ዓላማችን ነፋስ ተቀበላት
ብለን የምንቆመው ሰላም የምንላት
ፀጥታ ሲኖር ነው አልፈን በጦርነት፤
አንደኛው ሲተኛ ያኛው ሲጠብቀው
ሰላም ወይ ጦርነት ድርና ማግ ናቸው:
የተቀጣጠለው አንጩቱ እየጩሰ
መሬት ቁና ሁና የሰው ልጅ ሲጩንቀው
እሳት ተያይዞ አገሩን ሲያለብሰው
ባለቤት ተሰዶ አዱኛ ፈራርሳ
አሞራ ሲያንዣብብ ተከምሮ ሬሣ
ሥጋ ሲርበደበድ ነፍስ ይሸቆጠቆጣል
የኔ እያቀዘፈው ደም ይገነፍላል፡
ኮሽ ባለ ቁጥር ዞሮ ሲገላመጥ
እየተንሻተተ ገደሉን ሲባጥጥ
ሲቃትት ሲደክም ሲርበው ሲጠማው
ሥጋውን በመካድ ሞትን ይመኛል ሰው።
የፍቅር ጥላነው ጭጋግ የደስታ
ኀዘን መንገላታት፤ መታሠር መቸገር
መቁሰል መሰቃየት የሌለው ፀጥታ
ያንድነት እከክ ነው ልብሱ የነተበ
በላብ በጭቅቅት ገላው የረጠበ
ተለዋዋጭ መልኩ ያልታወቀ ግቡ
አልቋል ሞቷል ሲሉት ያው ይነትራል ልቡ።
ሥጋ ተለያይቶ ሲቀር አጥንታቸው
ማንንም በስሙ መጥራት የማንችለው
መልካቸው ሲጠፋ ሁነው እንዳልነበር
እነሆ ርስታቸው የእኩል ቤት መቃብር።
መድፍ የተከላቸው መትረየስ ዘርዝሮ
ቦምብ የመገባቸው አይሮፕላን በሮ፣
ታንክ በደነጎረው ጠመንጃ ዘርቷቸው
ጢስ ወሀ እየሆነ ሲጠጡ ባፋቸው
የታል የበቀሉት ወዴት ነው ቦታቸው?
ልምላሜአቸው የታል ፍሬያቸው የታለ?
ሐውልቱ ድንጋዩ ምን አጎነቆለ!
ባንድ በኩል ደግሞ
የሰላም ሚዛን ነው፤
የበዛን አረሞ
የሚያስተካክለው።:
ሰላም ብዙ ሲቆይ ሥሩ ይሻግታል
መሠረቱ ዝጎ ቀስ ብሎ ይወድቃል፤
አንስቶ በመካብ የፈራረሰውን
ቀብሮ በመለሰን ሲያድስ መሠረቱን፤
ኃይለኛ ሲገባ ሲከተል ዓላማ
ባላህ እርጋ ብሎ አዋጁን ሲያሰማ፤
ይኸው ተጀመረ አዲስ ዓይነት ሰላም
ዳገመኛ እስቲወድቅ ፈርሶ እስቲደመደም፤
ሰላም ያቻት ብሎ ሁሉም የሚጮኸው
ክፉ ቀን አታምጣ ብለን የምንተቸው፤
በፀሎታችን ውስጥ መሪ እንዳያሳጣን
ወድቀን እንዳንቀር ተገዥ በመሆን፤
ያቻት ዓላማችን ነፋስ ተቀበላት
ብለን የምንቆመው ሰላም የምንላት
ፀጥታ ሲኖር ነው አልፈን በጦርነት፤
አንደኛው ሲተኛ ያኛው ሲጠብቀው
ሰላም ወይ ጦርነት ድርና ማግ ናቸው: