ነፋስ ወይም አየር ወሀ ነሽ እንፋሎት
መልአክ ወይም ሰይጣን ብርሃን ወይም ጽ፳ጽልመት?
ድንጋይ፤ አፈር፤ ጭቃ፤ ቅጠል፤ አእንጩት፤ ልጥ
አልተረዳሁትም ሥራሽን በቅጥ።
ብረት፤ ነሐስ፤ መዳብ፣ ወርቅ፣ ሉል፤ አልማዝ፤
አገልጋይ ለሥራ ለጌጥ የሚያዝ?
ቀይ ነሽ ብጫ ነሽ፣ አረንጓዴ ጥቁር
ሐምራዊ ቡና ዓይነት ቀለምሽ የሚያምር?
ፉንጋ ነሽ ሰልካካ ቆንጆ ወይም መጥፎ?
የማር እንጀራ ነሽ የወጣ ከቀፎ:
ወለላው በጌሾ በውሀ ተጣርቶ
ናላዬን ያዞረው ከቦታው አናግቶ።
አጭር ነሸ እረጅም ወፍራም ወይ ቀጭን?
ወርድና ስፋትሽ ልኩ ምን ይሆን?
እያለሽ የለሸም ሳትኖሪም አለሽ
ጣፍጠሽ የምትመሪ ማርና እሬት ነሸ
የምታቃጥዩ ቃሪያ ነሽ በርበሬ
እሳት ለብላቢ ነሽ አከሰልሽኝ ዛሬ፡።
ነገ ስትሄጂ የለሁም ትቢያ ነኝ
ካንቺ ጋር ይጓዛል ሐሳቤ ሳይገኝ።
እርግጥ የፈጣሪ ነሽ ወይ እስትንፋስ?
እውነት ቀሪ ረቂቅ የማይዳሰስ
ኃይሌ ነሽ ምርኩዜ ብርታቴ ጤናዬ
ጠጉሬ፤ ግንባሬ ዓይንና አፍንጫዬ፡
አፌ ጆሮዬ ነሽ ጥርሴና ምላሴ
ሆድ ዕቃዬ ልቤ ሳምባዬ እስትንፋሴ፡
አንጎሌ ነሽ አንቺ የግሬ የጄ ጌታ
ደግፈሽ የያዝሽኝ የሆንሽኝ መከታ።
አልጋሽ ነኝ፤ ፍራሽሽ፤ መከዳ ልብስሺ
የምትዳስሺኝ ስትንቀሳቀሺ።
ጥላሽ ነኝ እርምጃሽ ግዞተኛ ላንቺ
ስለቀቅ የምሮጥ አስረሽኝ ስትፈቺ።
መኖርሺን እንጃ ስሜትሽ ሕልም ነው
የራቀው ሰማይ ነሽ የማይዳሰሰው።
የተረሳሽው ነሽ ያለፈው ትናንት
ማነው የሚያስብሸሽ አሌለሁበት?
ሽቱና ቅባትሽ የታለው መዓዛ?
የውሀ ሽታ ነው የተነሣው ለዛ።
ጌጥሽ ወዴት ይሆን ያለ ቅስቃሴ?
ገዳም የገባ ነው የሞተ መነኩሴ።
የምትጫወችው ሙዚቃው የታለ?
አፌና ምላሴ ድምጴም ዝም ካለ።
እኔ ነኝ የሆንኩት ሳላውቀው አንቺን
ለኔ ብዬ ላንቺ ጤና ስለምን።
በሓሳብ መሣሪያ የፈጠረኩሽ እኔ
ቦታም የሰጠሁሽ ፅድቅና ኩነኔ።
በቅርፅ አሳምሬ በቀለም ቀብቼ
የእግዚአብሔርን ፀዳል ብርሃኑን ሰርቼ፤
የኔ ማየት መስማት መሆኑን ሳላውቀው
ሳላውቀው መሆኑን ሐሳቤ በሞላው
የሳምባዬ ወናፍ የልቤ ጭፈራ
የደሜ መራሯራራጥ የጉበቴ ሥራ፤
አንጎሌ መንፈሴን እያውለበለበው
ትንፋሼ እሳቱን እያቀጣጠለው
ገላዬይ ሲጫጫስ ሲቃጠል ሲፍም
ስበላ ሲሞቀኝ ስሮጥ ስደክም፣፤
የፍጥረት ግዴታ አካሌን ሲያሠራው
እየቆሰቆሰ ሕይወት ሲመግበው፤
አለሁ ብዬ ሳስብ አንቺ ነሽ ምክንያት
ማነሸ በኑሮዬ ቤት የሠራሽበት?
ምንድን ነሽ? ምንድን ነሽ? ምንድን ነሽ? ምንድን ነሽ?
ካንቺ ጋር እያለሁ ሳውቀው የማላውቅሽ
ቅመም ነሽሸ ዝንዥብል ቅርንፉድ ቀረፋ
የነጠረ አረቄ የእህል አረፋ?
የሚያንገዳግደኝ እግሬን ያሳሰረው
ምንድን ነው ጥንስሱ ለይቼ ልወቀው?
ወዴት ነው ቀበሌሽ መደበቂያሽ ዋሻው?
ከልቤ ውስጥ ይሆን የሚንደፋደፈው?
ወይም ባዶ ቦታ ዓይን የማይደርስበት
ጫጫታ ሁካታ ጭጨኸት የሌለበት?
እንቆቅልሽ ነፍሴ ንገሪኝ በርጋታ
ጩንቆኛል ጠቦኛል ያለሽበት ቦታ።
ነፍሴ ተገለጪ መኖሬን ላስታውስ
የት እንደምትሔጂ?
የት እንደምትቀሪ?
ምን እንደምትፈቅጂ?
ምን እንደምትሠሪ?
ሲወሰድ ጀምሮ አብሮኝ የሚኖረው የሚንቀሳቀሰው
ይዝኸ ሰውነቴ ሲበተን ሲፈርስ፡
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ