ሁሉም ይለወጣል
ያለፈው ጩልሟል
ግልፅ ነው ዛሬ ቀን
መጭውን አናውቅም
አዲስ መንገድ አለ
ሰው ካዘነበለ
ወደ ስሜቱ ግብ ወደ ልቡ እርምጃ
ካየ፣፤ ካስተዋለ፤ ካሰበ፤ ከሔደ
መጥፎ ነው ያለውን ለምዶት ከወደደ
የሚፈልገውን አያጣውም እንጃ!
ምንድን ነው ብቻነት? እየኖሩ መጥፋት
ከሰው ማህል መውጣት
በሐሳብ ጎዳና መብረር መባከን
ለመያዝ መሞከር የማያዩትን
በኀዘን ምን አለ? ደስታስ ምንድነው
ሰመመን ትካዜ ምን መሠረት አለው?
ሳቅ፤ጩዋታ፤ ፍቅር፣ ምንድን ነው ዓይነቱ
ጥላቻና ቁጣ ወዴት ይሆን ቤቱ?
ይህ ሁሉ ሐሳብ ነው
ሐሳብ ግብ ይኑረው
ሔዶ ዞሮ ዞሮ ይመለስ ከቦታው
ይታይ መልኩ ይውጣ ይውረድ ክንብንቡ
ይናገር፥ ያስረዳ፥ ይገለጥ ጥበቡ
ሓሳብ ነው ሥራችን፤
ነው ሓሳብ ኑሯችን፣
አመል ጥብቆ ነው፤
ገላን የሚያለብሰው
የልጅነት አመል የልጅነት ልብስ፣
ሲያድጉ የሚቀር ነው የሚበጣጠስ፡
አዲስ ልብስ ይሰፋል፤
አዲስ እድገት ሞልቷል።፡።
ያልደረጀው ጊዜ ልጅ የሚኖርበት፤፣
ይሻራል፤ ይቀራል፤ ይረሳል ሲተውት።
የማኅበር ኑሮ
የዱሮውን ሽሮ
በሰፊው ይገልፃል፤ ብዙ ጓዝ ያመጣል፤
ማስተካከል ያሻል።
ከሚሮጠው ጋራ እርምጃቫን ማስገባት፤
ከሚቀመጠውም ሔዶ ቁጭ ማለት።
መሳቅ፤ መተዋወቅ፤ መጫወት፤ መውደድ' ነው፤
ጊዜ እንዳቀረበው።
ግዴታ ይመጣል፤
የማይፈልጉትን ጊዜ ያስለምዳል።
በሕይወት ሰንሰለት ሁላችንም ታሥረን
ስንኖር ልዩ ነን፣፤ ስናስብ ብዙ ነን፤
ስንሠራ ግብ አለን።
ያሻናል መሞከር፤
ማድረግ ወይ መናገር።
ሙከራ ነው ሕይወት፤
ብዙ ሳንክ ያለበት
ትልቁ ዳገት ላይ ትልቁ ቁልቁለት
ነው የሚያንሸራትት፤
ያኛው ይለቀቃል ይኸው ሲጩበጥ፤
በዚህ ይረገጣል በዚያኛው ሲቧጠጥ፤
ሲሔዱ የሜታይ ኋላም የሚረዱት፤
የሚያስተካክሉት፤
አንደኛው ሲያስቸግር ሌላው ጠቀለለ፤
የሚገለፅ አለ።
ይኸ ሲፈራርስ ያ ይመሠረታል፤
በዚያኛው ሲዘጋ በዚህ ይከፈታል፤
ሳይደክም የሮጠ ከግቡ ይደርሳል።
አለመሰልቸት ነው ማስቀረት ፍርሐትን፤
አለመተው ግብን።
ላቀዱት ዓላማ ፊትን ሳይመልሱ
መሥራት ነው መታገል ኃይል እስኪጩርሱ።
መታገሥ፤ መሞከር፣ ማሳለፍ፤ መጠበቅ፣
ሲናደዱ መሳቅ።
ፅድል ጉዞ ሲይዝ ሲጠፋ መከራ
የድካሙ ፍሬ ተለቅሞ የጠራ፤
ይሰጣል አዝሙራ።
ስለዚህ መሞከር መሞከር መድከም ነው፤
ስንኖር እንደሰው።
፡ ጋዜጣው "መውድ" ነው የሚለው።
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ