ያለም መራራነት ነው የሚጣፍጠን
መቸ መጣፈጧ፤
ኮሶውን በማሯ ጠቅልላ ስትሰጠን ስትሰጠን እአሳቱን
አመድ አስመስላ ሸፍና ረመጡን።:
ስትሰጥ ማየ ሕይወት ስትሰጠን መዳኀኒት
መርዚን ጩምራበት።
ስትሰጠን እሬቱን ስኳር አስመስላ
አእንደ ጎመን ሠርታ ሳማዋን ስንበላ፡
እሷ ትዞራለች
ፀሐይ ትሞቃለች
እኛን በብርድ ላይ በጩለማ ጥላ።
ያለም መራራነት
የሚያቆራምድ ነው፤ የሚያኮራምት።
ስትወስድ ወደ ኋላ፤ ስትወስድ ወደሌላ
ምሥጢር ያላት መስላ:
ከቤተሰብ ማህል
ሰው ስታስኮበልል።
ስትወስድ ስጦታዋን
ለገፀበረከት ያቀረበችውን።:
ሌባ ናት ሰራቂ
ቀጣፊ ነጣቂ።
አባባይ ቀልማዳ፤ አታላይ አስመሳይ
ዋሾ ናት ወላዋይ።
ሰው ሊኖር ባለም ላይ መቸ ተፈጠረ!
መንገደኛ እንግዳ
መሸቶበት የመጣ
ሠራተኛ አገልጋይ ነው የተቸገረ።
ብዙ ነው ልፋቱ
ሲፈጠር፥ ሲመጣ፥- ሲወጣ ከቤቱ።
አይችልም መፅናናት
በደመ ነፍስ ባህርይ እንደተቀረፁት።
እንዳህያ እንደጅብ ወይም እንደጦጣ
ወይም አንዳንበጣ
የማይቸገሩት ለምን ያስባሉ?
ከብቶች ይግጣሉ፤ ወፎች ይዘፍናሉ
አበቦች ያድጋሉ።
ውስጡን አላወቁም፤ አልእተመራመሩም
ሲመጡ ወዳለም
የውሸት ሥዕል ናት
ለዛዋ እሚጠፋ፤ ቀለሟ እሚጠፋ
ሽታዋ እሚሜጠፋ።:
ጠረኗ እሚያባርር፣ ጣሟ አእሚከረክር
ቧልቷ የሚያስመርር:
የሰው ልጅ አንድ ባንድ ልታንሸራሽረው
ሁልጊዜ እንግዳ ነው።
ማናፈስ ማቅበጧ
ማቻኮል ማሮጧ ፡
ያለም መራራነት ነው የሚጣፍጠን
መቸ መጣፈጧ!
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ