የሚስተካከልህ የሚያስንቅህ የለም።
ኀዘን የምታርቅ የገነት ምሳሌ።
ይታደል ወለላህ ጠጁ በብርሌ።
ይስከር በደስታ ሕዝቡ ይሳሳቅ፤
ድምፁ አየተማታ ሙዚቃው ይፍለቅ:
ፅንቁጣጣሽ ብለን እንስጥህ ሰላምታ፤
ይጩብጩብ ለዝናህ!
ይጩብጩብ ለሥራህ!
ይጩብጩብ ለመልክህ!
አንተ ነህ መስከረም።
ዘመን የምታድስ አስጊጠህ በቀለም።
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ