የዛፉ ቅርንጫፍ የበገና ቅኝት
ነፋስ ሲያውተረትር የሚጫወትበት ፡
አዎጩበጩቡ ፤
ቅጠሎች በጃቸው ዜማውን ሲያደምቁ
ወፎች ድምጻቸውን እያስረቀረቁ ፤
ወንዙ እየተላጋ ፤
እየተጋረፈ ሲሔድ አእንዳለንጋ ፣
ባሕር ሲገላበጥ
እየተንጠራራ ወደቡን ሲቧጥጥ ፤
መብረቅ ደመናውን ሰንጥቆ ሲወጣ
እያስገመገም ሰማዩ ሲቆጣ ፤
ሙዚቃ ተወልዷል ።:
ፍጥረት ተሰብስቦ መዝሙር ይዘምራል ፡
የቤቱን ቆርቆሮ
ዝናም ሲደበድብ አርጎታል ከበሮ ፡
ከሩቅ አገር አለ ደወል የሚመጣ
ከቤተ ክርስቲያን ተሰርቆ የወጣ ፤
ትንንሽ ደወሎች ፤
የሰዓት፣ የጥሪ፤ የተማሪ ቤቶች ፣
የቀጥቃጭ መዶሻ ብረት ሲያጠፈጥፍ ፤
ትልልቅ ፋብሪካ ጭሱ ሲያነፈንፍ፤
መኪና እየጮኸ ሲሔድ ሲተላለፍ ፤
ሁሉም ተሰብስቦ በቅደም ተከተል
ሙዚቃን ቀስቅሷል ፡
ሙዚቃ ተፈጥራል ፡
አለ ትልቅ ጆሮ ።
አለ ሌላ ጆሮ ።
ይህን ሁሉ ጨኸት ሰብስቦ አስተባብሮ
የሚሰማው አለ ፡
የሚወደው አለ ፡
ከቅርብ አውራ ዶሮ ሰዓቱን ሲያስታውስ ፤
ድመቶች ሲጣሉ፤
አራዊት ሲአስካካ ከብቱ በመላቀስ፤
እንጩት ሲገነጠል ሣሩ ሲርመሰመስ ፡
ለሙዚቃ ስልቱ
ድምፅ ነው የሚያግዝ ተጩማሪ ምቱ ፡
ጥቃቅን ፍጥረቶች
ትሎች፤ ሸረሪቶች፤ ጉንዳኖች፤ ቁጫጮች፤
ማነው ያዳመጠ ሲጮሁ ሲዘፍኑ?
ሰውም ባይሰማቸው ፤
የሚያዳምጣቸው፤
አለ ልዩ ጆሮ ፣
አለ ሌላ ጆሮ ፤
ዜማቸውን ይዞ የሚዘምር አብሮ ።
የሙዚቃ ድምፅ
አለ ሁሉም ቦታ፤ አለ የትም ቦታ፤
በቅጠል ኮሽታ ፤
በወሀ ጠብታ ፤
በንጋት በሌሊት በብርሃን በማታ፤
ወይ ከባዶ ቦታ።
ሲወለድ ይመጣል የሙዚቃ ስሜት
ከሰማይ ከመሬት።
ይህን ሁሉ ጨኸት ፡
አለ ትልቅ ጆሮ
አለ ሌላ ጆሮ
ለቅሞ አያከማቸ ሰብስቦ አስተባብሮ ፤
የሚሰማው አለ ፡
የሚወደው አለ ።:
ነፋስ ሲያውተረትር የሚጫወትበት ፡
አዎጩበጩቡ ፤
ቅጠሎች በጃቸው ዜማውን ሲያደምቁ
ወፎች ድምጻቸውን እያስረቀረቁ ፤
ወንዙ እየተላጋ ፤
እየተጋረፈ ሲሔድ አእንዳለንጋ ፣
ባሕር ሲገላበጥ
እየተንጠራራ ወደቡን ሲቧጥጥ ፤
መብረቅ ደመናውን ሰንጥቆ ሲወጣ
እያስገመገም ሰማዩ ሲቆጣ ፤
ሙዚቃ ተወልዷል ።:
ፍጥረት ተሰብስቦ መዝሙር ይዘምራል ፡
የቤቱን ቆርቆሮ
ዝናም ሲደበድብ አርጎታል ከበሮ ፡
ከሩቅ አገር አለ ደወል የሚመጣ
ከቤተ ክርስቲያን ተሰርቆ የወጣ ፤
ትንንሽ ደወሎች ፤
የሰዓት፣ የጥሪ፤ የተማሪ ቤቶች ፣
የቀጥቃጭ መዶሻ ብረት ሲያጠፈጥፍ ፤
ትልልቅ ፋብሪካ ጭሱ ሲያነፈንፍ፤
መኪና እየጮኸ ሲሔድ ሲተላለፍ ፤
ሁሉም ተሰብስቦ በቅደም ተከተል
ሙዚቃን ቀስቅሷል ፡
ሙዚቃ ተፈጥራል ፡
አለ ትልቅ ጆሮ ።
አለ ሌላ ጆሮ ።
ይህን ሁሉ ጨኸት ሰብስቦ አስተባብሮ
የሚሰማው አለ ፡
የሚወደው አለ ፡
ከቅርብ አውራ ዶሮ ሰዓቱን ሲያስታውስ ፤
ድመቶች ሲጣሉ፤
አራዊት ሲአስካካ ከብቱ በመላቀስ፤
እንጩት ሲገነጠል ሣሩ ሲርመሰመስ ፡
ለሙዚቃ ስልቱ
ድምፅ ነው የሚያግዝ ተጩማሪ ምቱ ፡
ጥቃቅን ፍጥረቶች
ትሎች፤ ሸረሪቶች፤ ጉንዳኖች፤ ቁጫጮች፤
ማነው ያዳመጠ ሲጮሁ ሲዘፍኑ?
ሰውም ባይሰማቸው ፤
የሚያዳምጣቸው፤
አለ ልዩ ጆሮ ፣
አለ ሌላ ጆሮ ፤
ዜማቸውን ይዞ የሚዘምር አብሮ ።
የሙዚቃ ድምፅ
አለ ሁሉም ቦታ፤ አለ የትም ቦታ፤
በቅጠል ኮሽታ ፤
በወሀ ጠብታ ፤
በንጋት በሌሊት በብርሃን በማታ፤
ወይ ከባዶ ቦታ።
ሲወለድ ይመጣል የሙዚቃ ስሜት
ከሰማይ ከመሬት።
ይህን ሁሉ ጨኸት ፡
አለ ትልቅ ጆሮ
አለ ሌላ ጆሮ
ለቅሞ አያከማቸ ሰብስቦ አስተባብሮ ፤
የሚሰማው አለ ፡
የሚወደው አለ ።: