ጠጉርሽን ዳብሶ በጆሮሽ ያለፈው
ነፋሱ ምን አለሽ?
በመስኮት ላይ ሆነሽ።
የፍቅሬን ሰላምታ ሲያስተጋቡ ይዘው
ተራሮች የላኩት፣
በሩቅ የሚታዩት።
የሚወዛወዙት ቆመው በመስኮትሽ
ዛፎቹ ምን አሉ?
ይንሾካሾካሉ።፡
አይተዋል ደብዳቤ ማታ ስጽፍልሽ
ይግለጹ ምሥጢሩን፤
ልቤ መሸበሩን።
ልብስሽን ስትለብሽ ወፎች የሚዘፍኑት
የሚሉት ምንድነው?
ጡቶችሽን አይተው:
በፍቅርሸ ሰላምታ ልቤን አንዲያክሙት
ላኪያቸው ያምጡልኝንሐ፤
መድኃኒቱን ይስጡኝ።
ኮከቦች ከሰማይ ይጠቃቀሳሉ
ውበትሽን አይተው፤
በቅርጽሸ ተደንቀው።
በሰማዩ ባሕር ጠልቀው ይዋኛሉ
ፍቅርሽን ሊይዙ
ወደኔ ሊጓዙ።
ምን አለች ጩረቃ በመስኮትሽ ገብታ?
ስትነካ ፊትሽን፤
ተደግፋ አልጋሽን።
ልኬልሽ ነበረ የፍቅር ሰላምታ
ጠይቂአት ውሰጂ፣
መልሱንም ስደጂ፡
የቤተ ክርስቲያን ደወሉ ዘመረ
ምን ሆኖ ይጮኻል?
ሰው ይሰበሰባል።
ጉዳችንን አይቶ ገልጦ ተናገረ
አባክሸ ለፍቅር
ሞተን አንቀበር።፡
ምነው ምን ፈለገ ሲጩፍር ከበሮ?
ተነሣ የሚለኝ?
'ጋዜጣው ላይ "የማታዩት" ነው የሚል። የኅትመት ስህተት ይሆናል በሚል ነው በድፍረት "ማ"ን ወደ "ሚ"
የለወጥኩት።
የሚቀሰቅሰኝ።፡
ፍቅርሽና ፍቅሬን በመሐረም አስሮ
እንሒድ ተቃቅፈን፤
ደብቆ ይውሰደን፤
የበረረው ልቤ ካጠገቤ ጠፍቶ
ምን ምሥጢር አወራ?
ደንግጦ አየፈራ፡
ስታንጎራጉሪ መኝታሽ ቤት ገብቶ
የፍቅሬን ሰላምታ
ይስጥሽ በቀስታ።
ነፋሱ ምን አለሽ?
በመስኮት ላይ ሆነሽ።
የፍቅሬን ሰላምታ ሲያስተጋቡ ይዘው
ተራሮች የላኩት፣
በሩቅ የሚታዩት።
የሚወዛወዙት ቆመው በመስኮትሽ
ዛፎቹ ምን አሉ?
ይንሾካሾካሉ።፡
አይተዋል ደብዳቤ ማታ ስጽፍልሽ
ይግለጹ ምሥጢሩን፤
ልቤ መሸበሩን።
ልብስሽን ስትለብሽ ወፎች የሚዘፍኑት
የሚሉት ምንድነው?
ጡቶችሽን አይተው:
በፍቅርሸ ሰላምታ ልቤን አንዲያክሙት
ላኪያቸው ያምጡልኝንሐ፤
መድኃኒቱን ይስጡኝ።
ኮከቦች ከሰማይ ይጠቃቀሳሉ
ውበትሽን አይተው፤
በቅርጽሸ ተደንቀው።
በሰማዩ ባሕር ጠልቀው ይዋኛሉ
ፍቅርሽን ሊይዙ
ወደኔ ሊጓዙ።
ምን አለች ጩረቃ በመስኮትሽ ገብታ?
ስትነካ ፊትሽን፤
ተደግፋ አልጋሽን።
ልኬልሽ ነበረ የፍቅር ሰላምታ
ጠይቂአት ውሰጂ፣
መልሱንም ስደጂ፡
የቤተ ክርስቲያን ደወሉ ዘመረ
ምን ሆኖ ይጮኻል?
ሰው ይሰበሰባል።
ጉዳችንን አይቶ ገልጦ ተናገረ
አባክሸ ለፍቅር
ሞተን አንቀበር።፡
ምነው ምን ፈለገ ሲጩፍር ከበሮ?
ተነሣ የሚለኝ?
'ጋዜጣው ላይ "የማታዩት" ነው የሚል። የኅትመት ስህተት ይሆናል በሚል ነው በድፍረት "ማ"ን ወደ "ሚ"
የለወጥኩት።
የሚቀሰቅሰኝ።፡
ፍቅርሽና ፍቅሬን በመሐረም አስሮ
እንሒድ ተቃቅፈን፤
ደብቆ ይውሰደን፤
የበረረው ልቤ ካጠገቤ ጠፍቶ
ምን ምሥጢር አወራ?
ደንግጦ አየፈራ፡
ስታንጎራጉሪ መኝታሽ ቤት ገብቶ
የፍቅሬን ሰላምታ
ይስጥሽ በቀስታ።