ወዴት አለ እንቅፋት |!
ለዚህ ትንሽ ተባይ ፤
መሬትን አስጊጦ ላደረጋት ገነት:
ባራት እግሩ ሲሔድ ባለም ላይ ገንፍሎ
ሲንፈፏቀቅ ሲጎተት ኋላም ብድግ ብሉ ፤
አንጎሉ ረቀቀ።
ማድረግ መፍጠር ቻለ እየተናነቀ።
በሥራው አደገ ፤ በአእምሮው አደገ፣፤
በሐሳቡ አደገ።
ዘልቆ እየጠለቀ በመመራመሩ ፤
ለውጥ እየፈለገ በመከራከሩ ፤
ሁሉንም በለጠ ።
ሁሉንም ጩበጠ ፡
የጥበብ ዕንቁላል አስኳሉ ፈረጠ
ቅርፍቱ ተሰብሮ ዛፉ ተመጠጠ ፡
የባሕር ሆድ ዕቃው ወጣ ተበዝብዞ ፤
ሰማይ ተሰንጥቆ ፤
ፅውቀት ይለቀማል በብልሃት ተይዞ።
የመሬት የውስጡ የሥር የማህሉ
አካባቢው ሁሉ ፤
ተጠና ታወቀ ኃይል እየተስፋፋ
ጉልበት ተከማቸ መሰናክል ጠፋ ፡
አቶም ተነቆረ !
አየር መጋረጃው በሰው ተበገረ ።:
መች እንዲህ ሆነና
ይራመዳል ገና።
ከተማውን ሠርቶ ይኖራል በሰማይ
ባዶ ቦታ ሔዶ ይዘረጋል ድልድይ ፡
የስልኩ ማዞሪያ " አሎ ጩረቃ " ነው
ቁርሱ ከማርስ ላይ ከቪነስ ላይ ምሳው ፣
ከመሬት አእራቱን ፤
በልቶ ይጩፍራል ሜርኩሪ ላይ ዳንሱን :
የብርሃንን ፍጥነት ሲሽቀዳደም ይዞ
ከመ ቅጸበተ ዓይን ይሔዳል ተጉዞ ።
ያንዱ ኮከብ መቅናት ለሌላው መረጃ
ሆኖ መራመጃ ፤
ዓየርን ይተዋል ሲፋጠን ወደላይ
ዓለማት ተገዝተው ይጠበዋል ሰማይ ።
ሁሉን ይለውጣል ።
ለማየት ለመስማት ፤ ለማሽተት ለመንካት፤
ለጣም አዲስ ዓይነት ፤
ሥያሜ መጠሪያ መንገድ ይሰጠዋል ።
ባዶ ቦታ ሆኖ ፈጥሮ መገናኛ
በሴኮንድ መቶኛ ፤
ሁሉንም ይሠራል ፡
የጥበብ ምዕራፍ አዳዲስ ይሆናል ፡
ከሌላው ዓለም ላይ መከላከያውን
ፈጥኖ ይጋፈጣል ፡
የፀሐይን ፀሐይ ፣ የፀሐይን ፀሐይ፣
ይኸ ትንሽ ተባይ !
በሥልጣኑ ገዝቶ ያስገብራቸዋል ።
መሬት ስታበራ ከጩረቃ ዛፍ ሥር
ይፈጥራል ሙዚቃ ቅኔ ሲደረድር ።
ያገኛል መድኃኒት
ሲኖር በከዋክብት ፡
ሞትን ያሸንፋል !
ሁሉን ሲቆጣጠር . . . ይሆናል :
ወዴት አለ እንቅፋት !
የት አለና ዳገት !
ለዚህ ትንሽ ተባይ ፡
ገና ይራመዳል ፡
ከጀርመን አገር
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ