ሀቻምና በረረ፣
አምናም ተሻገረ፤
ዘንድሮም ይሮጣል፤
ሕፃን እያደገ ልጅ ይጎለምሳል።
ይጠፋል አሮጌው ወጣት እያረጀ፣
ጊዜ እየደረጀ።
ተከማችቶ አይሞላም፤
እንደምን በረረ፤ ይገርማል! አይቆምም።
መስከረም ሲቀባ ቀለም ባመት ባመት፤
አልተወም ማደሱን ያረጀውን ፍጥረት
ያደፈውን መሬት፣፤
ክረምትም ሲገባ ማጠቡን በውሀ፤፣
በተራው ሲተካ በጋም ከበረሃ፣
አልተወም ይለፋል፣፤
ሁሉም ይንፈፏቀቃል፤
ገመዱን ሲጎትት ጊዜ ይቀልዳል።:
ምን ይሆን ይኸ ጊዜ?
የሰዓት እጆቹ ድምፁ ውዝዋዜ።
ወይም የሰው ዕድሜ ሰብዓና ሰማኒያ፤
ያመት መለወጫ የዘመኑ ጣቢያ።
ወይ ቀንና ሌሊት፣
ወይ መወለድ መሞት፤
ወይም ያለም መዞር የፀሐይ መታየት፣
ሙሉዋ ጩረቃ፤ የጩረቃ መጥፋት።
ጊዜ ይኸ ይሆን?
ሰው ነው የሚሔደው ጊዜን እየለካ?
ወይስ ጊዜ ቆሟል ምንም ሳይነካ?
ምናልባትም ደግሞ አብረው ይሔዳሉ፣
እየተቻኮሉ፤
ወደኋላው ሲቀር ፍጥረት በድካሙ፣
ጊዜ ይራመዳል ሲቃለል ሸክሙ።
ባንድ በኩል ደግሞ ጊዜ ፍፁም የለም፣
መነሻ መድረሻ መካከል የለውም:።:
ሰው ነው የሚለካው፣፤
ፀጥታን ሰንጥቆ ድምፅ እንደሚወጣው።
ጩለማን ሲረታ፤
ብርሃን እንደሚገኝ በጠቆረው ቦታ።
ሰው በጊዜ ላይ፤
ይሆናል መስታዎት መኖሩን የሚያሳይ።
አእንዳይሆን ያስፈራል!
ይኸም አንዳይባል፤
ሰው ቢኖር ባይኖርም መሬት መሽሸከርከሯን፣
ወር አእየቆጠረች ጩሬረቃም መውጣቷን፤
ባህር መላወሱን፥ ዝናም መርከፍከፉን፤
አፈር መንፈቀቁን፤
አይተውም ሥራውን ምንም አያቋርጥ
ሰው ነው ተመልካቹ በዘመን ላይ ሲሮጥ።
ውሸት ነው ይጠፋል!
ጊዜም እንደሌላው፤
ጊዜም ከሚወደው፤
ጊዜም ከጊዜው ጋር ሞቶ ይቀበራል።
ፍ ቹ #
የነቢያት ጊዜ ዛሬ ወዴት አለ?
የነቄሳር ጊዜ ዛሬ ወዴት አለ?
ጄንጂስካን ግዛቱ፤
የሂትለር ኩራቱ፤
ዛሬ ወዴት አለ?
ቅኝ አገር መሻማት ዛሬ ወዴት አለ?
የመርከብ ወንበዶች ጊዜአቸው የታለ?
እንደ ዱሮ አይሆንም
ታሪኩ ቢወራ ሐተታው ቢለቀም፤
አእንደ ጥንቱ አይሆንም።
መሰሉም ቢመጣ ጥቂት ተለውጦ፤
ያለፈውን ጊዜ ጭራውን ቆንጥጦ።
"ታሪክ ተደገመ"
ይባላል ሲጠፋ ጊዜ እየታመመ
በራሱ ከረጢት ገብቶ ተጠቅልሎ፤
ለብቻው ሲደበቅ ሸሸቶ ተገልሉ፤
አስታዋሽ ሲያገኘው፤
እየታየ ጥላው።
ሁሉም ይለወጣል ጊዜ እየቆጠረ
አንዳንዴም ይረሳል እየተሰወረ
ጩረቃ እንደክብሪት ፀሐይ አእአንደሻማ
በርተው ይጠፋሉ፤
ተቃጥለው ያልቃሉ።
ሰማይ ተቀዳዶ እንዳሮጌ ሸማ
ከዋክብት አንድ ባንድ ወድቀው ተንጠባጥበው
የባህርይ ፍጥረቶች እንዳልነበር ሆነው
ሲመጣ ጊዜአቸው ፤
ያልፋሉ ጩልመው።
የማያልፍ ምን አለ?
የማይቀር ምን አለ?
ሞትም ሙት ይሆናል የሚሞት ሲጠፋ፤
ጊዜም እየገፋ
የሚገፋው ሲያጣ ይሆናል የጠፋ።
አምናም ተሻገረ፤
ዘንድሮም ይሮጣል፤
ሕፃን እያደገ ልጅ ይጎለምሳል።
ይጠፋል አሮጌው ወጣት እያረጀ፣
ጊዜ እየደረጀ።
ተከማችቶ አይሞላም፤
እንደምን በረረ፤ ይገርማል! አይቆምም።
መስከረም ሲቀባ ቀለም ባመት ባመት፤
አልተወም ማደሱን ያረጀውን ፍጥረት
ያደፈውን መሬት፣፤
ክረምትም ሲገባ ማጠቡን በውሀ፤፣
በተራው ሲተካ በጋም ከበረሃ፣
አልተወም ይለፋል፣፤
ሁሉም ይንፈፏቀቃል፤
ገመዱን ሲጎትት ጊዜ ይቀልዳል።:
ምን ይሆን ይኸ ጊዜ?
የሰዓት እጆቹ ድምፁ ውዝዋዜ።
ወይም የሰው ዕድሜ ሰብዓና ሰማኒያ፤
ያመት መለወጫ የዘመኑ ጣቢያ።
ወይ ቀንና ሌሊት፣
ወይ መወለድ መሞት፤
ወይም ያለም መዞር የፀሐይ መታየት፣
ሙሉዋ ጩረቃ፤ የጩረቃ መጥፋት።
ጊዜ ይኸ ይሆን?
ሰው ነው የሚሔደው ጊዜን እየለካ?
ወይስ ጊዜ ቆሟል ምንም ሳይነካ?
ምናልባትም ደግሞ አብረው ይሔዳሉ፣
እየተቻኮሉ፤
ወደኋላው ሲቀር ፍጥረት በድካሙ፣
ጊዜ ይራመዳል ሲቃለል ሸክሙ።
ባንድ በኩል ደግሞ ጊዜ ፍፁም የለም፣
መነሻ መድረሻ መካከል የለውም:።:
ሰው ነው የሚለካው፣፤
ፀጥታን ሰንጥቆ ድምፅ እንደሚወጣው።
ጩለማን ሲረታ፤
ብርሃን እንደሚገኝ በጠቆረው ቦታ።
ሰው በጊዜ ላይ፤
ይሆናል መስታዎት መኖሩን የሚያሳይ።
አእንዳይሆን ያስፈራል!
ይኸም አንዳይባል፤
ሰው ቢኖር ባይኖርም መሬት መሽሸከርከሯን፣
ወር አእየቆጠረች ጩሬረቃም መውጣቷን፤
ባህር መላወሱን፥ ዝናም መርከፍከፉን፤
አፈር መንፈቀቁን፤
አይተውም ሥራውን ምንም አያቋርጥ
ሰው ነው ተመልካቹ በዘመን ላይ ሲሮጥ።
ውሸት ነው ይጠፋል!
ጊዜም እንደሌላው፤
ጊዜም ከሚወደው፤
ጊዜም ከጊዜው ጋር ሞቶ ይቀበራል።
ፍ ቹ #
የነቢያት ጊዜ ዛሬ ወዴት አለ?
የነቄሳር ጊዜ ዛሬ ወዴት አለ?
ጄንጂስካን ግዛቱ፤
የሂትለር ኩራቱ፤
ዛሬ ወዴት አለ?
ቅኝ አገር መሻማት ዛሬ ወዴት አለ?
የመርከብ ወንበዶች ጊዜአቸው የታለ?
እንደ ዱሮ አይሆንም
ታሪኩ ቢወራ ሐተታው ቢለቀም፤
አእንደ ጥንቱ አይሆንም።
መሰሉም ቢመጣ ጥቂት ተለውጦ፤
ያለፈውን ጊዜ ጭራውን ቆንጥጦ።
"ታሪክ ተደገመ"
ይባላል ሲጠፋ ጊዜ እየታመመ
በራሱ ከረጢት ገብቶ ተጠቅልሎ፤
ለብቻው ሲደበቅ ሸሸቶ ተገልሉ፤
አስታዋሽ ሲያገኘው፤
እየታየ ጥላው።
ሁሉም ይለወጣል ጊዜ እየቆጠረ
አንዳንዴም ይረሳል እየተሰወረ
ጩረቃ እንደክብሪት ፀሐይ አእአንደሻማ
በርተው ይጠፋሉ፤
ተቃጥለው ያልቃሉ።
ሰማይ ተቀዳዶ እንዳሮጌ ሸማ
ከዋክብት አንድ ባንድ ወድቀው ተንጠባጥበው
የባህርይ ፍጥረቶች እንዳልነበር ሆነው
ሲመጣ ጊዜአቸው ፤
ያልፋሉ ጩልመው።
የማያልፍ ምን አለ?
የማይቀር ምን አለ?
ሞትም ሙት ይሆናል የሚሞት ሲጠፋ፤
ጊዜም እየገፋ
የሚገፋው ሲያጣ ይሆናል የጠፋ።