ማሸነፍ ምንድን ነው?
የምኞት አዝመራ
የደስታ መከር፣፤
የታጩደ ጣጣ
የተወቃ ችግር፤
የሞተ መከራ፤
የሚነድ እሳት ነው ተዳፍኖ የበራ።
አእያደር ጠፊ ነው፤
እያደር ቀሪ ነው ሲቆይ ይሰለቻል፣፤፣
ዋጋው ይቀንሳል።
ሁልጊዜ በማግኘት፤
ዘወትር በማሸነፍ ዘወትር በመመከት፤
በመግዛት በመቅጣት፤
ደስታ አይገንኝም።
ሌላ ይፈልጋል የሰው ልብ አይጠግብም።
ለጥቅሙ የሚያስብ የተስገበገበ፤
መንገዱን የማያቅ ግቡ የጠበበ፤
ስስታም ይሆናል
ለፍቶ ጥሮ ግሮ ሲያጋጥመው ዕድል።
ፅረፍት አያገኝም፤
ሲያስብ፥ ሲያጠነጥን፤ ሲታትር፣ ሲደክም፤
አንዱን በመጩጨረስ ወጥኖ ሌላውን፤
ያንን በመሰልቸት ሲጀምር አዲሱን፤
ያቅበዘብዘዋል፤
ትዕግሥት ይነሳዋል።
ትንሽ መሰናክል እሾህ መንገዱ ላይ፤
የኑሮው ሕመም ነው የሕይወቱ ሥቃይ፤
ያገባዋል እልክ ደሙን አስቆጥቶ፣
ንዴቱን አምጥቶ
ይተዋል ይሉኝታን ከግቡ ለመድረስ፤
ወዲያ ወዲህ ብሎ ኃይሉን እስኪጩርስ
በመሸነፍም ነው፤
ሰው ደስታ ያለው።
በመተው በመርሳት፤
በመልቀቅ በማጣት፤
በመሸሽ በመፍራት።
ወደፊት ከመሔድ አውቆ በማፈግፈግ፤
ከማሰብ ለብዙ ጥቂት በመፈለግ፤
በማነስ ከማደግ።
በመጣል ከማንሳት፥ በመስጠት ከመውሰድ፤
በማልቀስ ከመሳቅ፤ በመቅረት ከመሔድ፤
ከመውጣት በመውረድ፡።
ከመልበስ መታረዝ፤
ከማምለጥ በመያዝ።:
ክብርን ለመጠበቅ ደፍሮ ከመናገር
አንገት በማቀርቀር።
በመዋረድና በችግር ተጎድቶ፤
በመውደቅ ተገፍቶ፤ በመናቅ ተጠልቶ፤
በኀዘን፤ በድካም፣ በሕመም፤ ባርምሞ
አግኝቶ በመክሰር፤ በመሻር ተሹሞ
ያውቃል ማ መሆኑን፤
ይረዳል አቅሙን።
የሕይወት ለውጥ ነው ያለ በኑሮ ላይ፤
እንደ ቀን፣ እንደ ሌት ፣ እንደመሬት ሰማይ፤
እንደ ውሀ አንደሳት እንደልቅሶ ሳቅ፤
እንደርጥብ ደረቅ፤
ሁሉም ተለውጦ አንፃሩን ይይዛል፤
የሚሮጠው ጊዜ ጥቂት ይታገሣል ።
ሰዓቱ ይቆማል፤
ደቂቃው ይተኛል።
ይሸፈናል ወሩ፤
ይታሠራል ቀኑ፤
ቀስ ይላል ዘመኑ።
የሚፈጥነው ሐሳብ ከጉዞው ሲመለስ፣
ያንዣብባል መንፈስ፣፤
የምትራወጠው ትቀመጣለች ነፍስ።
አጥንትና ጡንቻ፤
ጅማትና ሥጋ፣
ዝለው ይወድቃሉ፤
ሰላም ያገኛሉሌ።
ፅረፍትና ድካም ያሳዩታል ቤቱን፤
ይተኛል ዕንቅልፉን፤
ሲያውቀው መሸነሩን።
የምኞት አዝመራ
የደስታ መከር፣፤
የታጩደ ጣጣ
የተወቃ ችግር፤
የሞተ መከራ፤
የሚነድ እሳት ነው ተዳፍኖ የበራ።
አእያደር ጠፊ ነው፤
እያደር ቀሪ ነው ሲቆይ ይሰለቻል፣፤፣
ዋጋው ይቀንሳል።
ሁልጊዜ በማግኘት፤
ዘወትር በማሸነፍ ዘወትር በመመከት፤
በመግዛት በመቅጣት፤
ደስታ አይገንኝም።
ሌላ ይፈልጋል የሰው ልብ አይጠግብም።
ለጥቅሙ የሚያስብ የተስገበገበ፤
መንገዱን የማያቅ ግቡ የጠበበ፤
ስስታም ይሆናል
ለፍቶ ጥሮ ግሮ ሲያጋጥመው ዕድል።
ፅረፍት አያገኝም፤
ሲያስብ፥ ሲያጠነጥን፤ ሲታትር፣ ሲደክም፤
አንዱን በመጩጨረስ ወጥኖ ሌላውን፤
ያንን በመሰልቸት ሲጀምር አዲሱን፤
ያቅበዘብዘዋል፤
ትዕግሥት ይነሳዋል።
ትንሽ መሰናክል እሾህ መንገዱ ላይ፤
የኑሮው ሕመም ነው የሕይወቱ ሥቃይ፤
ያገባዋል እልክ ደሙን አስቆጥቶ፣
ንዴቱን አምጥቶ
ይተዋል ይሉኝታን ከግቡ ለመድረስ፤
ወዲያ ወዲህ ብሎ ኃይሉን እስኪጩርስ
በመሸነፍም ነው፤
ሰው ደስታ ያለው።
በመተው በመርሳት፤
በመልቀቅ በማጣት፤
በመሸሽ በመፍራት።
ወደፊት ከመሔድ አውቆ በማፈግፈግ፤
ከማሰብ ለብዙ ጥቂት በመፈለግ፤
በማነስ ከማደግ።
በመጣል ከማንሳት፥ በመስጠት ከመውሰድ፤
በማልቀስ ከመሳቅ፤ በመቅረት ከመሔድ፤
ከመውጣት በመውረድ፡።
ከመልበስ መታረዝ፤
ከማምለጥ በመያዝ።:
ክብርን ለመጠበቅ ደፍሮ ከመናገር
አንገት በማቀርቀር።
በመዋረድና በችግር ተጎድቶ፤
በመውደቅ ተገፍቶ፤ በመናቅ ተጠልቶ፤
በኀዘን፤ በድካም፣ በሕመም፤ ባርምሞ
አግኝቶ በመክሰር፤ በመሻር ተሹሞ
ያውቃል ማ መሆኑን፤
ይረዳል አቅሙን።
የሕይወት ለውጥ ነው ያለ በኑሮ ላይ፤
እንደ ቀን፣ እንደ ሌት ፣ እንደመሬት ሰማይ፤
እንደ ውሀ አንደሳት እንደልቅሶ ሳቅ፤
እንደርጥብ ደረቅ፤
ሁሉም ተለውጦ አንፃሩን ይይዛል፤
የሚሮጠው ጊዜ ጥቂት ይታገሣል ።
ሰዓቱ ይቆማል፤
ደቂቃው ይተኛል።
ይሸፈናል ወሩ፤
ይታሠራል ቀኑ፤
ቀስ ይላል ዘመኑ።
የሚፈጥነው ሐሳብ ከጉዞው ሲመለስ፣
ያንዣብባል መንፈስ፣፤
የምትራወጠው ትቀመጣለች ነፍስ።
አጥንትና ጡንቻ፤
ጅማትና ሥጋ፣
ዝለው ይወድቃሉ፤
ሰላም ያገኛሉሌ።
ፅረፍትና ድካም ያሳዩታል ቤቱን፤
ይተኛል ዕንቅልፉን፤
ሲያውቀው መሸነሩን።