ሰው ፤ ግሩም ሰው አንተ !
ለመጀመሪያ ነው ፣
የሰው ልጅ በሕይወት ጥሎ የተለየ
መሬትን ከውጭ እየዞረ ያየ
የስፔትኒክ በራሪ ፤
በሰማይ በራሪ በብረት በራሪ
ምንም ይሁን ማንም
ስም ዋጋ የለውም ።
አንደኛው ምዕራፍ ይኸው ተከፈተ ፤
ሰው ሰማይ ዳበሰ
ሰው ዓለምን ጥሎ ሔደ ተመለሰ
ሕልም እውነት ይሆናል
ሰው ይክበር ይመስገን የሰው ልጅ ይሞገስ
ለሰው መዝሙር ይውጣ ለሰው ልጅ ይደክስ ፤
ጎረቤቶቻችን ፤ በሌላው ዓለማት ውሸት ነው አይኖሩም ፤
ከረቀቀው ባሕርይ ከሰው ልጅ አእምሮ
በልጠው የሚገኙ በጥበብ በኑሮ
እርግጥ ቢሆን ኑሮ
( እስከ ዛሬ ድረስ ከሰው ልጅ ቢበልጡ )
ይችሉ ነበረ ጩረቃን ሊረግጡ
ይችሉ ነበረ መሬትን ሊረግጡ
ወደኛ ሊመጡ እኛን ሊጩብጡ
እልክ ነው ፣ ወኔ ነው ፣
የሰው ልጅ ኩራት ነው ፣
የሰው ልጅ ዕድገት ነው ፣
ጥበብ ጉድ ነገር ናት
ውበት ጉድ ነገር ናት
ሰው የሚደነቅ ነው !
የዘመን ላይ ጤዛ የመሬት እንጉዳይ
የጊዜ አዋራ የማያርፈው ተባይ
ሰው ውበት
ሰው ጥበብ ፣
ሰው ፣ ግሩም ሰው አንተ !
ይቅናህ በመንገድህ
የሰው ልጅ ምንጊዜም ጥበብ አይለይህ ፣
እንግዲህ ከዋክብት
እመኑ ገብሩ
ላዲሱ እንግዳ ሰማያት ዘምሩ
ሒድ የሰው ልጅ ድረስ
ዓለማትን አይተህ ከመሬት ተመለስ ፣
ይቅናህ በመንገድህ
ፍቅር ጥላ ሲጥል'
በገና
ቢቃኙ ፤
ሸክላ
ቢያዘፍኑ
ክራር
ቢጫወቱ ፣
ለሜሚወዱት
ምነው
ሙዚቃ
ቢመቱ ፤
ቢቀኙ
ቢያዜሙ ፤
ቃል
ቢደረድሩ ፤
ጌጥ
ውበት
ቢፈጥሩ ፤
ቤት
ንብረት
ቢሠሩ ፤
አበባ
ቢልኩ ፤
ምነው
ቢናፍቁ !
አገር
ቢያቋርጡ
ቢሔዱ
ቢርቁ ፤
ዓመት
ቢጠብቁ
ዘመን
ቢጠብቁ ።
ለሚወዱት ምነው....
' ጣው ላይ ' ፪ቆቅርጥሳሲጥል” ነሠ የሟል። ጋዜጣው ላይ በዚህ መልክ የተፃፈው በቦታ
ጥበት ምክንያት ስለመሰለኝ ብቻ ነው ያስተካከልኩት። ምን ማለቴ እንደሆነ ለመመልከት የሚሹ አንባብያን
ጋዜጣውን እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ።
ለመጀመሪያ ነው ፣
የሰው ልጅ በሕይወት ጥሎ የተለየ
መሬትን ከውጭ እየዞረ ያየ
የስፔትኒክ በራሪ ፤
በሰማይ በራሪ በብረት በራሪ
ምንም ይሁን ማንም
ስም ዋጋ የለውም ።
አንደኛው ምዕራፍ ይኸው ተከፈተ ፤
ሰው ሰማይ ዳበሰ
ሰው ዓለምን ጥሎ ሔደ ተመለሰ
ሕልም እውነት ይሆናል
ሰው ይክበር ይመስገን የሰው ልጅ ይሞገስ
ለሰው መዝሙር ይውጣ ለሰው ልጅ ይደክስ ፤
ጎረቤቶቻችን ፤ በሌላው ዓለማት ውሸት ነው አይኖሩም ፤
ከረቀቀው ባሕርይ ከሰው ልጅ አእምሮ
በልጠው የሚገኙ በጥበብ በኑሮ
እርግጥ ቢሆን ኑሮ
( እስከ ዛሬ ድረስ ከሰው ልጅ ቢበልጡ )
ይችሉ ነበረ ጩረቃን ሊረግጡ
ይችሉ ነበረ መሬትን ሊረግጡ
ወደኛ ሊመጡ እኛን ሊጩብጡ
እልክ ነው ፣ ወኔ ነው ፣
የሰው ልጅ ኩራት ነው ፣
የሰው ልጅ ዕድገት ነው ፣
ጥበብ ጉድ ነገር ናት
ውበት ጉድ ነገር ናት
ሰው የሚደነቅ ነው !
የዘመን ላይ ጤዛ የመሬት እንጉዳይ
የጊዜ አዋራ የማያርፈው ተባይ
ሰው ውበት
ሰው ጥበብ ፣
ሰው ፣ ግሩም ሰው አንተ !
ይቅናህ በመንገድህ
የሰው ልጅ ምንጊዜም ጥበብ አይለይህ ፣
እንግዲህ ከዋክብት
እመኑ ገብሩ
ላዲሱ እንግዳ ሰማያት ዘምሩ
ሒድ የሰው ልጅ ድረስ
ዓለማትን አይተህ ከመሬት ተመለስ ፣
ይቅናህ በመንገድህ
ፍቅር ጥላ ሲጥል'
በገና
ቢቃኙ ፤
ሸክላ
ቢያዘፍኑ
ክራር
ቢጫወቱ ፣
ለሜሚወዱት
ምነው
ሙዚቃ
ቢመቱ ፤
ቢቀኙ
ቢያዜሙ ፤
ቃል
ቢደረድሩ ፤
ጌጥ
ውበት
ቢፈጥሩ ፤
ቤት
ንብረት
ቢሠሩ ፤
አበባ
ቢልኩ ፤
ምነው
ቢናፍቁ !
አገር
ቢያቋርጡ
ቢሔዱ
ቢርቁ ፤
ዓመት
ቢጠብቁ
ዘመን
ቢጠብቁ ።
ለሚወዱት ምነው....
' ጣው ላይ ' ፪ቆቅርጥሳሲጥል” ነሠ የሟል። ጋዜጣው ላይ በዚህ መልክ የተፃፈው በቦታ
ጥበት ምክንያት ስለመሰለኝ ብቻ ነው ያስተካከልኩት። ምን ማለቴ እንደሆነ ለመመልከት የሚሹ አንባብያን
ጋዜጣውን እንዲመለከቱ እጋብዛለሁ።