እንቅልፍህን ተኛ
የዘላለም እንቅልፍ.....
እንዳይቀሰቅሱ - ህ ።
የዚህ ዓለም ፀሐይ የሚያጭበረብረው
ዓይንህን አይንካው፡። የዚያን ዓለም ስቃይ
የዚያን ዓለም እንቅልፍ የሚያባንነውን
አእርሳው የኔ አባባ :
ጨኸቱን አትስማ ፡ ከበሮ ጸናጽል ፤
ፍታቱን ልቅሶውን ፤
ደረት ሲጠፈጠፍ ጠጉር መነጩቱን
አፈሩ ሲካበድ የድንጋዩን ጭነት
ግባ ተመሬቱን ፤
አእርሳው አባባዬ ፡
አታስብ ይበቃል !
ዱሮም አንተ እንደዚህ ብዙ ጊዜ አይተሀል ፡
አንተም አባት ሞቶህ፣
አንተም እናት ሞታህ ፤
ወንድም እህት ጠፍቶህ ፤
ሜስት የልጆች እናት.....
አንባህን ጠርገሀል ፡
ታውቃለህ ብዙ ነው ፤ መንገዱ ብዙ ነው።
ሞት አንደንቆቅልሽ ፤
ጅምሩ ማለቂያው ፣
መካከሉ ዳር ነው።
ታውቃለህ ሰው ኢምንት ፤
ሰው ጥቃቅን ነገር ፣
ሲኖር የማይታይ፤
በሚሊዮን አጥፍ ፤
በሚሊዮን ጊዜ በጣም ካላጎሉት :
(ታውቃለህ የኔ አባት አስተምረኸኛል)
በመኖር በመሞት ፤
ልዩነት የሌለው ፣
ቢኖርም ልዩነት ፤
ከነፋስ ከውሀ መልኩ የቀጠነ
ዓይን የማይጩብጠው ፤
! የጋዜጣ ቦታ ለማብቃቃት ሲባል አንዳንዱ ስንኝ ተጩናንቆ የታተመ ይመስለኛል፡ፁ: ኦርጅናሌውን ፈልጎ
ለማስተካከል መሞከር ያስፈልጋል።
ሕይወትን ሲያነቡት ወደ ግራ ሞት ነው ።
(ብለህ ነግረኸኛል ።
ስለዚህ ግድየለም ።
እንቅልፍህን ተኛ ።
በጸጥታ ቦታ ካሳብ አልፎ ተርፎ ሐሳብ
ይኖር ይሆን ?
ግድ የለም !
ግድ የለም !
መመርመር አትሞክር ።
አንተው ሁን ፀጥታ !
ሕይወት የዘራውን የጤና ቡቃያ
በበሸታ አመዳይ ሞት እንደሚያጠፋው
በወዲያኛው ዓለም የፀጥታን ክዳን
ቢኖር ልዩ ነገር የሚቀሰቅሰው
አትንቃ ከንቅልፍህ !
በመብረቅ ነጎድጓድ ዓለም ይደባለቅ
ሰማይ መጋረጃው ይተርተር ይሰንጠቅ
ፀሐየ ፀሐያት ኮከብ ይንጠባጠብ ፤
ጩለማም ይጩልም ዓይን አውቆ እስኪጠፋ ፤
መሬት ጭቃ አዛባ እንደ ሊጥ ትበጥበጥ
ሌዋታን'- ይንቀጥቀጥ !
ብሔሞት” ይንቀጥቀጥ !
ሳጥናኤል ይቆጣ ሲኦል? አፉን ይክፈት
አልፍ ዓለም ይቃጠል በገሀነመ ሳት ፤
መንግሥተ ሰማያት ባልማዝ ሉል ታብረቅርቅ ፤
ገነት ትፍካ ትሳቅ !
ጉዳይህ አእንዳይሆን !
ዱሮ በልድነት.. . . . በጎልማስነቴ... .
አደንቅህ ነበረ ።
ያ ድምፅ የውቀት ደወል !
የሃይማኖት ዜማ የሕይወት ሙዚቃ
ኃያል ግርማ ሞገስ !
! "ሌዋታን፣... የባሕር አውሬ እንስሳ ፣ ዘንዶ ፥ ታላቅ ዓሣ ፣ ማናቸውም። እንስት ዐንበሪ ምድርን እነደ
ዝናር እነደ ጋን ሰንበር ፥ ወይም እነደ ቀለበት እንዳንባር ዙራ ተጠምጥማ ዐቅፋ የያዘች የብሄሞት ዘውግ
፥ ጣምራው ኹለተኛው ፣ ዘሩ ለወየ ነው ፣ ሌዋ ዐቃፊ ተጠምጣሚ ፣ ታን ዘንዶ ፥ ወይም ወርድና ቁመት
ግዘፈ ምድር።። በተገናኘ የምድር መታጠቂያ ቅናት መቀነት ማለት ነው።..." (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፥ 1948፥
፪ፅ፲፰፰፭፭ጓ በቁሙ ፣ የየብስ ዐንበሪ ከባሕር ተፈጥሮ በየብስ የሚኖር ፣ ግሩማን አራዊት የሚፈሩትና
የሚገዙት ከአራዊት ኹሉ የሚበልጥ መጩረሻ ግዙፍ ፥ የእንስሳት ራስ የአራዊት ንጉሥ ፣ በኩራቸው
ቀዳማያቸው ፣ በተፈጥሮ የሌዋታን ወንድም ባሏ መሰሏ ፡ ... ባለብሉዮች ግን ዝዣፕን ይሉታል ፡ " (ኪዳነ
ወልድ ክፍሌ፥ 1948፥ ገፅ 257)።
? ጋዜጣው "ሶኦል" ነው የሚለው። ግጥሙ ፍች ሊኖረው የሚችለው "ሲኢል" በሚል ከተስተካከለ ብቻ
ነው። የትየባው ስህተት የደረሰው "ሳኦል" ለማለት ሲሞከር ነው እንዳይባል ደግሞ " ሳኦል ፤ የሰው
ስም ፤ በእስራኤል ላይ መዥመሪያ የነገሠ ንጉሥ" መሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ ይታወቃል፣ ደስታ ተክለ
ወልድም በጥቅሱ ውስጥ ይህንኑ ነው የገለፁት (ዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት፥ 1962፥ ገፅ 1154)።
ያ በሰው ልጅ አምሳል የተጎናፀፍከው ።
አስተዋይነትህ።
አደንቅህ ነበረ !
ዱሮ በንግግር ፤ ዱሮ በትምህርት
ጥበብ ዕውቀት ሆነህ ፤
ፀሐይ ብርሃን ሆነህ ።
አሁን ጊዜው ሲመሸሽ.....
የድሜ ሳት ተቃጥሎ ከሰል ሲሆን ሕይወት
አሁን በዝምታህ ፤
አሁንም አያለሁ ፤
አያለሁ በፊትህ ዓይኔ በንባርሶ
የውበት ፈገግታህ አልጠፋም ጩርሶ ።
ትዝታሀ አልጠፋም
ደግነትህ አለ :
ፅውነቱ ክርስቲያን ዕውነቱ ሳምራዊ
ያ ቅዱስ ትህትናህ ፤ ቅዱስ ሰማያዊ :
ድካምክን አውቃለሁ ።. .
ድካምህ ልፋትሀ ፤ ላገር ለወገንህ ፤
ለሕግ ለነፃነት !
ለምነትህ ለውነትህ !
ሳቅ አሁንም በሞት ፤
/እዚህ የሌለ ሳቅ/
በፀጥታው ቦታ ሙዚቃ ሁንበት ፤
/ዝም ያለ ሙዚቃ/
አረፍት አድርግ አሁን ።
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ