ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አዕላፍ ሌሊት ፤
ሚሊዮን መሰለኝ
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ ቀኑ ረዘመብኝ ።
እኔ ወድሻለሁ
የሰማይ መሬቱን ፤
የባሕር ስፋቱን
እንዳለም ዳርቻ የርቀቱን ያህል ፡
አንደ ጽጌረዳ
እንዳደይ አበባ ፤
እንደ ሎሚ ሽታ ፤
እንደ ከርቤ ብርጉድ ፣ እንደጣን ጭስ እአንጩት
ውድ እአወድሻለሁ
አበባ እንዳየ ንብ ፤
እንደ ቢራቢሮ ጫካ እንደ ሚያስሰው
ፍቅርሽን በፍቅሬ በፍቅርሸሽ ልቅመሰው ።
ማር ወለላዬ ነሸ ከረሜላ ስኳር
አማርኛ አይበቃ
(ወይ ጉድ ! )
ባለም ቋንቋ ሁሉ ቢወራ ቢነገር ።
እኔሄ እወድሻለሁ ፡
እንደ ማታ ጀንበር ፤
አእንደ ጩረቃ ጌጥ ፤
እንደ ተወርዋሪ ኮከብ የማልጠግብሽ
ስወድሽ ፣ ስወድሽ ፣
ስወድሽ ፤ ስወድሽ ።
ጡት እንዳየ ሕፃን ወተት እንዳማረው
ጠጋ በይ ዘመዴ አፍሽ ሕይወቴ ነው ።
ጣይ ላይ ያለ ቅቡ-........
ገላዬ ገላሽን ሲነካ የሚያልቀው
አፈር መሬት ትቢያ ውሀ እንደሚበላው
ፍቅሬ አንቺን ስወድሽ............
ብዙ ሺህ ዘመናት
እልፍ አእላፍ ሌሊት ፣
ውድ እወድሻለሁ ፡
ዓይኖችሽን ባይኔሄ - ተዳክሜ እያየሁ ።
ስወድሽ ፣ ስወድሽ ፣
ውድ እወድሻለሁ ፡
፡ ጋዜጣው ላይ "ያለቅቤ" ተብሎ ነው የታተመው። ስህተት ስለመሰለኝ ነው ያስተካከልሁት:
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ