ሰው ፣ ሰው መሆኑን ........
ሰው ፤ ሰው መሆኑን የሚያሳውቅ ከሆነ ፣ በጭካኔ ሞት
ኦ ! ሞት ስጠኝ እስከ ዘላለም- ሞት የሞት ሞት :
ምን የህልፈተ ዓለም ጥሩንባ----ምን የጥፋት ከበሮ
ምን የክፋት ወጥመድ የቀጋ ሾህ፣ ዓለምን በሙሉ አስሮ
ምን ሙኸት ያሰማናል በየደቂቃው አርምጃ
ያቶሚክ ቦምብ ያዳፍኔ ...........
የተወሳሰበ ሙዚቃ ድምፅ ፤ የመትረየስ ወይ የጠመንጃ
የተጠላለፈ ሕይወት ሐረግ የመሠሪነት ሥጋጃሻ :
ምን መርዝ የባብ ጭንቅላት !
የገበሎ ራስ ናዜራ ፣ የፉኝት ምራቅ ነቀርሳ
ምን ስራስር ያረግ ሬሳ !
ምን የምድር እምቧይ የጠጅ አሰር ፣
የድፍድፍ አንቃር ያተላ
ምን የደም እርሾ ኮምጣጣ ፣ የሚንተከተክ የሚፈላሳ ፤
ዋጊኖስ' እጸ ዘዌ' ፤ የፍልፈል አፈር ፈልፈላሳ !
ያንዱ ሞት የሌላው ሕይወት .............
ያንዱ መኖር የሌላው መጥፊያ ፡
ጥሩ ሙዚቃ፣ ጥሩ ሙዚቃ ! ግሩም ማለፊያ፤ግሩም ማለፊያ
አቤት ! እገዚኦ ፤ አቤት !
ቪየትናም የቪየትናም ህልቂት'" ፤ናጋሳኪ የሂሮሺማ መጥፋት
ሻርፕቪል--ሞት የሞት ሞት
የሬሳ ክምር መዓት !
የሰው ልጅ ጥፋት መቃብር ፣ የሰው ልጅ መኖር ወይ አለመኖር
የሰው ክፋት ትል የማይሞት ፤ የሰው ተንኮል መርዝ የማይበገር
ጥቁር ቀይ ፤ ቀይ ጥቁር ፤
ነጭ ጥቁር ፣ ብጫ ነጭ ቀይ ፤
ድብልቅልቅ ውጥንቅጥ ፤
ከሰማይ በታች ከመሬት በላይ ፡
ያንዱ ሞት የሌላው ሕይወት...................
በግ ይታረዳል ሠንጋ ይጣላል የሠርግ ድግስ ዕልልታ
የደም ጠጅ መርዝ ስካር ፤ ከንቱ ሙዚቃ ኳኳታ
ከንቱ ያለም መሽከርከር ከንቱ ፣ የሌላው ዓለም ዓለም
ትቢያ የትቢያ ትቢያ--ኢምንት ቅንጣት ሰውር ፍጽጹም።
ሕይወት አበባ ፳ጌረዳ ፤
' "ዋጊኖስ ፤ ... ሥሩና ፍሬው ለደም ለተቅማጥ መድኀኒት ይኾናል፡ ቅጠሉም ቀጥቅጦ በውሃ ዘፍዝፎ
ብልትንና ዐይንን እንዳይነካ ተጠንቅቆ ገላን ቢቀቡት ከዕከክ ያድናል፡ ፪ኛ ስሙ ጉፋ ይባላል:' (ደስታ
ተክለ ወልድ፥1962፥ ገፅ 411)
" "ዘዌ ፤ የዛፍ ስም፣ የመርዝ መድኀኒት የሚኾን ዕንጩት..." (ደስታ ተክለ ወልድ፥ 1962፥ ገፅ 482)
? "እልቂት" ማለቱ ነው።
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ