በግሬ ጣራ መርገጥ ፣
ሙዚቃ ሲጋልብ መውጣት መውረድ
መፍረጥ ፤
ዓይኔን ማገላበጥ ፤
መርበትበት መንቀጥቀጥ ፤
መላጋት መንገድገድ እንደሰከረ ሰው
የናፈቀኝ ይህ ነው ፣
ተነስቼ ልዝለል ፤
" ቡጊ ቡጊ " ልበል ።
ቡጊ ! ቡጊ ! ቡጊ !
ቡጊ! ቡጊ ! ቡጊ !
ከበሮ ሲያጋፍት ጥሩንባ ሲያናፋ
ልብሴን ጥዬ ልጥፋ ።
ልራቆት አብጄ
ልብረር ካለም ሄጄ ፡
ሙዚቃው በጥላው ይምጣ ይሸፍነኝ
ሁሉንም ያስረሳኝ ።
ቡጊ ቡጊ ልበል
እንደሳት ቡግ ቡግ
መውለብለብ መንተግተግ
መቃጠል መሞቅ ነው
ሲጀምር ሙዚቃው ።
ጉልበቴ ይላላል ፤ አእግሬ መሬት ያካል ፤
ዛር ይሰፍርብኛል ።:
ጅማቴ እየዛለ ይለቃል ሙላዬ ፤
አንገቴ ሲሰበር ወርዶ ትከሻዬ ።
ይረግጣል ዳንኪራ
ከከበሮው ጋራ
ቡጊ! ቡጊ! ቡጊ!
ልስበቀው ጀርባዬን ፣
ልወርውር እጆቼን ፣
ልመንጭር ጣቶቹን ፣
ሙዚቃን እንደ ኳስ ልለጋው በእግሮቼ
ልዝለል ተነስቼ ።:
ልፍረጥ ፣ ልናር ፣ ልውደቅ ፣
መሬት ልንከባለል
ቡጊ! ቡጊ ! ልበል ፣
ልዝለል ጮቤ ልምታ
ያቃዣኝ አንዳፍታ ፡
ሙዚቃ ሲጋልብ መውጣት መውረድ
መፍረጥ ፤
ዓይኔን ማገላበጥ ፤
መርበትበት መንቀጥቀጥ ፤
መላጋት መንገድገድ እንደሰከረ ሰው
የናፈቀኝ ይህ ነው ፣
ተነስቼ ልዝለል ፤
" ቡጊ ቡጊ " ልበል ።
ቡጊ ! ቡጊ ! ቡጊ !
ቡጊ! ቡጊ ! ቡጊ !
ከበሮ ሲያጋፍት ጥሩንባ ሲያናፋ
ልብሴን ጥዬ ልጥፋ ።
ልራቆት አብጄ
ልብረር ካለም ሄጄ ፡
ሙዚቃው በጥላው ይምጣ ይሸፍነኝ
ሁሉንም ያስረሳኝ ።
ቡጊ ቡጊ ልበል
እንደሳት ቡግ ቡግ
መውለብለብ መንተግተግ
መቃጠል መሞቅ ነው
ሲጀምር ሙዚቃው ።
ጉልበቴ ይላላል ፤ አእግሬ መሬት ያካል ፤
ዛር ይሰፍርብኛል ።:
ጅማቴ እየዛለ ይለቃል ሙላዬ ፤
አንገቴ ሲሰበር ወርዶ ትከሻዬ ።
ይረግጣል ዳንኪራ
ከከበሮው ጋራ
ቡጊ! ቡጊ! ቡጊ!
ልስበቀው ጀርባዬን ፣
ልወርውር እጆቼን ፣
ልመንጭር ጣቶቹን ፣
ሙዚቃን እንደ ኳስ ልለጋው በእግሮቼ
ልዝለል ተነስቼ ።:
ልፍረጥ ፣ ልናር ፣ ልውደቅ ፣
መሬት ልንከባለል
ቡጊ! ቡጊ ! ልበል ፣
ልዝለል ጮቤ ልምታ
ያቃዣኝ አንዳፍታ ፡