ግማሸሽ ቀልድ አላውቅም!
ሞት እንደሆን ልሙት በሲኮንድ መቶኛ
እንቅልፍ እንደሬሳ ዘላለም ልተኛ ፡
መንገድ ስጡኝ ሰፊሬ ፤
ጉዞ ከጽንፍ አጽናፍ ፣
ፍጥነት እንደ ብርሃን ዓለማትን ልለፍ ።
ፀሐይ ልሁን ፀሐይ ፤
እንደ- ጽርሐ አርያም'- ሁሉንም የሚያሳይ ።
አሳተ ገሞራ አመድ እረመጡን ፤
ጎርፍ ፤ ሳት ጎርፍ ልሁን ።
ከሲኦል ሚሊዮን ቢሊዮን ልቃጠል ፤
ከገሀነመ እሳት ሚሊዮን ነበልባል ፡
መንገድ ስጡኝ ሰፊ---
ልሒድ በጩለማ ዓይን የማያይበት ፤
ጥቁር የከሰለ ፤ በጠቆረው ጽ፳ጽልመት ፤
በጸጥታው ቦታ ዘመን ከቆመበት ፡
በዘላለማዊው ባዶ ቦታ ዋሻ ፣
አየር በሌለበት አድማስ መጩረሻ ።
ልንሳፈፍ ልቃኘው ፤
ለኔ ኮከብ ጠጠር ኳስ መጫወቻ ነው ።
ቱ* ቹ ፏ
ሰው ነው የረቀቀ !
ከሜርኩሪ ቪነስ ፤
ከጩረቃ ከማርስ ፡
ከፕሉቶ ኔፕቱን ዑራነስ የላቀ ፣
ከጁፒተር ሳተርን ፀሐይ የደመቀ ፤
ባካባቢው ሁሉ እያሸበረቀ።
'"ጽርሐ አርያም ፤ በአርያም ያለ የብርሃን አዳራሽ። አርያምን ተመልከት።" (ደስታ ተክለ ወልድ፥ 1962፥
ገፅ 1020)። "አርያም ፤ የሰማይ ስም ፤ መጩረሻ ሰማይ። ዘሩ በግእዝ ረዬም ሬመ ነው።' (ደስታ ተክለ
ወልድ፥ ገፅ 137)፡
ሰው አደገ አወቀ ፤
መሬት ዕንቁላሉን ሰበረ መጠዋቀ ፡
ሰው ዓለምን አየ !
በጩለማው ቦታ ዶቃ አንፀባራቂ ፤
ውብ ሰማያዊ ኳስ ፣ ውብ ሮዝ አብረቅራቂ ፡
በተጣራው አየር በነጣው ደመና ፣
ባረንጓዴ እጣቢ ውሀ ተሸፍና ፡
ውብ ሉል ኮከብ ዓለም ፣
የጠፈር ላይ ጤዛ ፤
የሰው ልጆች እናት ፤ የሰው ልጆች ቤዛ ።
ቱ* ቹ ፏ
የመሬት ቁራጭ ንኝኝ ፤
ታሪኳን የምጽፍ ፤
በጥቁር ወረቀት በሰማይ ብራና ፣
ስጓዝ አእተዋለሁ በጠፈር ላይ ፋና ።
ስሔድ አእኖራለሁ.............
ሰማየ ሰማያት እመዘብራለሁ ፤
የተዘጋውን በር አበረግዳለሁ ፡
የሌለ እስቲፈጠር ፤ የሞተ አስኪነቃ ፤
በትልቅ እርምጃ ከመሬት ጠረቃ ፤
ከጩረቃ ኮከብ ፤
ካንዱ ዓለም ወዳንዱ ፤
ስንጓዝ አፈጥናለሁ... .
በፀሐይ ላይ ቤቴን ጎጆ እቀልሳለሁ ።
ግማሽ ቀልድ አላውቅም !
ከሲኦል ሚሊዮን ቢሊዮን ልቃጠል ፡
ከገሀነመ እሳት ሚሊዮን ነበልባል ፡
መንገድ ስጡኝ - --
ገብረ ክርስቶስ ደስታ ግጥሞች መስከረም 1947 – ነሐሴ 1961 · በፈቃደ አዘዘ