ኣብ
✦
ይህ ቁርባን ክቡር ነው ፍጹም ሰማያዊ ፪
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ ፪
ዋ ምን አፍ ነው የሚቀበለው
ዋ ምን ጥርስ ነው የሚያላምጠው
ዋ ምን ሆድ ነው የሚሸከመው
ነበልባል ያለበት የሚያቃጥለው
በንጽህና ሆኖ ላልተቀበለው
የሚያፍገመግም የሚጎዳ ነው
አምላካችን ሆይ አንተ ይቅር ባይ
እንደ ቸርነትህ በደልን አትይ ፪
አሜን አሜን ብለህ ተቀብለናል
በድፍረትም ሳይሆን በፍርሃት ቀርበናል ፪
ማክበር ይገባናል በንጽህና ሆነን
ደፍረን አናቅለው እንዳያቃጥለን ፪
እንደምታዩትም ይህ ቁርባን ፈራጅ ነው
እንደ ሌላ ሳይሆን የተቀደሰ ነው ፪
ሱራፌል ኪሩቤል ጸወርተ መንበር
ለመያዝ ያልቻሉት ፈርተውት በክብር ፪
እኛም ተመገብነው አገኘን ድህነት
ለነፍስ ለስጋችን ሆነልን ሕይወት ፪
እንዳይመስለን ተራ አይደለም ምድራዊ ፪
ዋ ምን አፍ ነው የሚቀበለው
ዋ ምን ጥርስ ነው የሚያላምጠው
ዋ ምን ሆድ ነው የሚሸከመው
ነበልባል ያለበት የሚያቃጥለው
በንጽህና ሆኖ ላልተቀበለው
የሚያፍገመግም የሚጎዳ ነው
አምላካችን ሆይ አንተ ይቅር ባይ
እንደ ቸርነትህ በደልን አትይ ፪
አሜን አሜን ብለህ ተቀብለናል
በድፍረትም ሳይሆን በፍርሃት ቀርበናል ፪
ማክበር ይገባናል በንጽህና ሆነን
ደፍረን አናቅለው እንዳያቃጥለን ፪
እንደምታዩትም ይህ ቁርባን ፈራጅ ነው
እንደ ሌላ ሳይሆን የተቀደሰ ነው ፪
ሱራፌል ኪሩቤል ጸወርተ መንበር
ለመያዝ ያልቻሉት ፈርተውት በክብር ፪
እኛም ተመገብነው አገኘን ድህነት
ለነፍስ ለስጋችን ሆነልን ሕይወት ፪
✦