አበባ ነሽ ድንግል

አበባ ነሽ ድንግል ምሳሌ የሌለሽ
አባ ሕርያቆስ የመሰከረልሽ
በጥሩ መዓዛሽ አብ እንደወደደሽ
ፍሬሽም ይለያል በብዙ ምክንያት
ከሚያፈሩት ፍሬ ሌሎቹ ዕጽዋት
በሽታን አጥፍቶ ስለሚሰጥ ሕይወት
አሁን ግን ከፊቱ ተለወጠ መልክሽ
በግበጽ በረሀ ሙቀት ሲበዛብሽ
ጥምሽን የሚቆርጥ ውኃ በማጣትሽ
ይህንን በማሰብ ይህን በመዘከር
በዕለተ ሰንበት በዚህ በጽጌ ወር
ቀርበናል ከፊት አሁን ለመዘመር
← መዝሙር