አበባን በሜዳ
✦
አበባን በሜዳ የሚያፈካ
ዘመንን በዘመን የሚተካ
የሚለዉጥ በጋ ክረምትን
እግዚአብሔር ይመስገን ፪
ዘመንን በዘመን የሚተካ
የሚለዉጥ በጋ ክረምትን
እግዚአብሔር ይመስገን ፪
ወራትን በክረምት አሰናድቶ
አሮጌዉን ዘመን አሰናብቶ
ፀሃይን ሲያወጣ በጊዜያቱ
ድንቅ ነዉ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ፪
አሮጌዉን ዘመን አሰናብቶ
ፀሃይን ሲያወጣ በጊዜያቱ
ድንቅ ነዉ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ ፪
ሰማይን በደመናት አልብሶ
ምድርን በነጠብጣብ አረስርሶ
ልምላሜን የሰራ በጊዜያቱ
መጋቢ ነዉ አምላክ ለፍጥረቱ ፪
ምድርን በነጠብጣብ አረስርሶ
ልምላሜን የሰራ በጊዜያቱ
መጋቢ ነዉ አምላክ ለፍጥረቱ ፪
አበቦች በተራራ ሲያበሩ
አእዋፍ ስለክብሩ ዘመሩ
ጸሐይም በሰማይ ስትወጣ
ደስ አለን አዲስ አመት ሲመጣ ፪
አእዋፍ ስለክብሩ ዘመሩ
ጸሐይም በሰማይ ስትወጣ
ደስ አለን አዲስ አመት ሲመጣ ፪
ሰማይን በደመናት አልብሶ
ምድርን በነጠብጣብ አረስርሶ
ምድርን በነጠብጣብ አረስርሶ
✦