አበረታኝ ፍቅርህ

አበረታኝ ፍቅርህ ጌታዬ
አበረታኝ ክንድህ አምላኬ
በስምህ ድኛለሁ በፀጋህ
በማደሪያህ ሆኜ ስጠራህ
አ.ዝ-----------------------
ሰዶም ስትቃጠል መርገሟ ሲበዛ
ሊተወኝ አይሻም ልጁን እንደዋዛ
ህጉን በማሰቤ አምላክ ፈረደልኝ
ጎትቶ የሚያወጣ መልአክ ሰደደልኝ
አ.ዝ-------------------------
በገናን መደርደር አያቆምም ጣቴ
የወንጭፌ ድንጋይ አንተነህ ጉልበቴ
የሳኦልን ካባ አውልቀህ ጣልክልኝ
የፍልስጤሙን ሰው ክንድህ ሰበረልኝ
አ.ዝ----------------------
ሶስት ጌዜ ስክድህ አላውቅህም ብዬ
ዶሮ ስለጮኸ ትዝ አልከኝ ጌታዬ
ወጣሁኝ በዕንባ ከአይሁድ እሳት ሥር
ከሐዲ ሳትለኝ አኖርኝ በፍቅር
አ.ዝ-------------------------
ሳምራዊ ናት ሳትል ክብርን የጠኽኝ
እንደ አንተ ከአይሁድ ፍቅርን ማን አሳየኝ
ምስጢሬን በሙሉ ነገርከኝ ጌታዬ
የፍቅር ውሃ ቀዳሁ እንሥራዬን ጥዬ
← መዝሙር