አቤት የዚያን ጊዜ

አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ
ትንሹም ትልቁም መድረሻውን ሲያጣ
ከምሥራቅ ከምዕራብ ከሰሜን ከደቡብ
አየራት ሲላኩ መላእክት ሲላኩ መዓትን ለማዝነብ
ሰማይና ምድር በአንድ ሲዋሃዱ
የት ይሆን መድረሻው የት ይሆን መንገዱ
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ
ትንሹም ትልቁም መድረሻውን ሲያጣ
ጻድቃን በቀኝ በኩል ኃጥአን በግራ
ሲነፋ መለከት ሲደለቅ እንዚራ
ምድር ቀውጢ ስትሆን አጥንት ሲሰበሰብ
ኀፍረት ይይዘዋል ሰው ለፍርድ ሲቀርብ
አቤት የዚያን ጊዜ ክርስቶስ ሲመጣ
ትንሹም ትልቁም መድረሻውን ሲያጣ
ጩኸት ሲበረታ የማይጠቅም ለቅሶ
እንደ ቁራ ጠቁሮ ጽልመትን ተላብሶ
ገነትን ሲያገኙ ጻድቃን በሥራቸው
ኃጥአን ወደ ሲዖል ተፈረደባቸው።
← መዝሙር