አቤቱ አቤቱ ኃጢአቴ

አቤቱ አቤት ኃጢአቴ ብዛቱ
መስፊሪያም የለውም እርስ ካልተወኝ በቸርነቱ
ከእኔ ኃጢአት ይልቅ ይበዛል ምሕረትህ
አደራ እንድትምረኝ ጌታ በቸርነትህ
እስከ አንገቴ ደርሶ የኃጢአቴ ብዛት
ሊውጠኝ ነውና አውጣኝ የእኔ አባት
ለእግሬ መቆሚያ ከሌለው ባሕር
ድረስልኝ ጌታዬ ወድቄ እንዳልቀር
ወደአንተ ስጣራ በጩኸት ደክሜ
ተስፋ ሊያስቆርጠኝ የኃጢአት ሸክሜ
ወደ ኃላ ልቤ እንዳይመልስኝ
መልካም እረኛዬ አንተ ጠብቀኝ
የሠራሁት ሁሉ ከአንተ አይሰወርም
ይቅር ትለኛለህ አልጠራጠርም
መመለሴን እንጂ መሞቴን አትወድም
በዚህ እጽናናለሁ ከፍቅርህ አልርቅም
አንተን ስበድልህ ይቅር እንዳልከኝ
የሚበድሉኝን ይቅር በልልኝ
ይቅርታ ለማድረግ እኔን ቢከብደኝ
አንተ አይቸግርህም ይቅርታ ስጠኝ
← መዝሙር