አቤቱ አንተን እጠራለሁ
✦
አቤቱ አንተን እጠራለሁ
ነፍሴን ወዳንተ አነሳለሁ
ዝም አትበለኝ እጮሀለሁ ፪
ነፍሴን ወዳንተ አነሳለሁ
ዝም አትበለኝ እጮሀለሁ ፪
የሐጢያት ሸክሙም ከብዶኛል
የሥጋ ወጥመድም አስሮኛል
የሰይጣን ሽላግ አጥቅቶኛል ፪
የሥጋ ወጥመድም አስሮኛል
የሰይጣን ሽላግ አጥቅቶኛል ፪
ደካማ ነኝ በጣም ችግረኛ
ምስኪን ተስፋ-ቢስ አመጸኛ
ከመንጋው የራቅኩኝ ብቸኛ ፪
ምስኪን ተስፋ-ቢስ አመጸኛ
ከመንጋው የራቅኩኝ ብቸኛ ፪
ሐጢያቴን ሁሉ ይቅር በለኝ
የንስሀን በር ክፈትልኝ
መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ ፪
የንስሀን በር ክፈትልኝ
መጣሁኝ ጌታ ተቀበለኝ ፪
የቤትህ ናፍቆት አቃጠለኝ
የቃልህ በረከት ራበኝ
እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ ፪
የቃልህ በረከት ራበኝ
እባክህ ጌታ ይቅር በለኝ ፪
ከአንተ ኮብልዬ ተንከራተትኩ
ምንም ላይረባኝ ከንቱ ባከንኩ
ለበስባሽ ሥጋዬ ተገዛሁ ፪
ምንም ላይረባኝ ከንቱ ባከንኩ
ለበስባሽ ሥጋዬ ተገዛሁ ፪
✦