አቤቱ በመንግሥትህ

በመንግሥትህ አስበኝ
በበደሌ ብዛት አይተህ አትጣለኝ
ሳስበው በደሌ ብዙ ነው
በጨለማ ነፍሴን በላት ውድማ
ሆዴ ባባ አፈሳለሁ እንባ
እርቃኔን ቀረሁኝ ተገፈፈ ልብሴ
መድረሻው ጠፋብኝ ተጨነቀች ነፍሴ
የብርሃን ጸዳሌ ከዓይኔ ተገፈፈ
ከፊትህ ለመቆም ጉልበቴ ታጠፈ
አልቻልኩም ደግፈኝ እንድቆም
ለገነት የበቃ ያቀማኛ ሽፍታ
እኔንም ደግፈኝ አውጣኝ የዚያን ለታ
← መዝሙር