አቤቱ ማረን ይቅር በለን
✦
አቤቱ ማረን ይቅር በለን ፪
ያለአንተ መድኃኒት የለን፪
ሥጋዬን ብሉና ደሜን ጠጥታችሁ
ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኑራችሁ
አቤቱ -----------------
ብሎ ነበር እርሱ የሚሰማው ጠፋ
ሁሉም በየድርሻው ምኞቱን ሲያስፋፋ
አቤቱ -------------
በሕይወት ለመኖር ትእዛዙን ጠብቀን
ምኞት ሳነበዛ እናስብ ስሙን
አቤቱ ------------
በሥጋው ቀድሶ ሲያድነን በደሙ
ምን ውለታ ሠራን ለአምላክ በስሙ
አቤቱ --------------------
ይህን ቅዱስ ሥጋ ይህን ክቡር ደም
እንዴት ልጆች ብቻ በልተውት ይፈጸም
አቤቱ ------------------
ብዙ ሰው ለግብዣ ተጠርቶ ነበረ
ጊዜን በማሳለፍ ከዚያው ከደጅ ቀረ
አቤቱ -----------------
ሌሎቹ በጥበብ ለመዳን ሲደክሙ
ሕይወት የተገኘው በሥጋ ወደሙ
አቤቱ --------
ያለአንተ መድኃኒት የለን፪
ሥጋዬን ብሉና ደሜን ጠጥታችሁ
ዘለዓለማዊ ሕይወት ይኑራችሁ
አቤቱ -----------------
ብሎ ነበር እርሱ የሚሰማው ጠፋ
ሁሉም በየድርሻው ምኞቱን ሲያስፋፋ
አቤቱ -------------
በሕይወት ለመኖር ትእዛዙን ጠብቀን
ምኞት ሳነበዛ እናስብ ስሙን
አቤቱ ------------
በሥጋው ቀድሶ ሲያድነን በደሙ
ምን ውለታ ሠራን ለአምላክ በስሙ
አቤቱ --------------------
ይህን ቅዱስ ሥጋ ይህን ክቡር ደም
እንዴት ልጆች ብቻ በልተውት ይፈጸም
አቤቱ ------------------
ብዙ ሰው ለግብዣ ተጠርቶ ነበረ
ጊዜን በማሳለፍ ከዚያው ከደጅ ቀረ
አቤቱ -----------------
ሌሎቹ በጥበብ ለመዳን ሲደክሙ
ሕይወት የተገኘው በሥጋ ወደሙ
አቤቱ --------
✦