አዳም ሆይ
✦
አዳም ሆይ እህት አገኘህ፪
በሐሴት ይሙላ ልቡናህ ደስ ይበልህ
ሔዋን ሆይ ወንድም አገኘሽ፪
በሐሴት ይሙላ ልቦናሽ ደስ ይበልሽ
ብቻህን መሆንህን እግዚአብሔር አይቶ
የከበደ እንቅልፍን በአንተ ላይ አምጥቶ
አጥንት ወሰደና አንዷን ከጎንህ
እህት እንድትሆንህ ሔዋንን ሰጠህ
ሄዋን ሆይ ……
ከጎኑ ተፈጥረሽ በሥላሴ ጥበብ
አክብሪው ባልሽን ተዋደዱ ከልብ
አዳም ከጎንሽ ነው የሚያስብልሽ
የአምላክን ስጦታ ውሰጅው ፈቅደሽ
አዳም ሆይ----------
አካልህ ሔዋን ናት የአንተ እጣ ፈንታ
አምላክ ባረካችሁ በብዙ ደስታ
የኑሮ ተካፋይ አምላክ ከሰጠህ
ሕይወቴ ነች ብለህ ሂድ ወደ ሚስትህ
በሐሴት ይሙላ ልቡናህ ደስ ይበልህ
ሔዋን ሆይ ወንድም አገኘሽ፪
በሐሴት ይሙላ ልቦናሽ ደስ ይበልሽ
ብቻህን መሆንህን እግዚአብሔር አይቶ
የከበደ እንቅልፍን በአንተ ላይ አምጥቶ
አጥንት ወሰደና አንዷን ከጎንህ
እህት እንድትሆንህ ሔዋንን ሰጠህ
ሄዋን ሆይ ……
ከጎኑ ተፈጥረሽ በሥላሴ ጥበብ
አክብሪው ባልሽን ተዋደዱ ከልብ
አዳም ከጎንሽ ነው የሚያስብልሽ
የአምላክን ስጦታ ውሰጅው ፈቅደሽ
አዳም ሆይ----------
አካልህ ሔዋን ናት የአንተ እጣ ፈንታ
አምላክ ባረካችሁ በብዙ ደስታ
የኑሮ ተካፋይ አምላክ ከሰጠህ
ሕይወቴ ነች ብለህ ሂድ ወደ ሚስትህ
✦