አዳምን ሊያድነው
✦
አዳምን ሊያድነው ጌታችን ወደደ
ነፍስና ሥጋሽን ነስቶ ተዋሐደ
በአባቱ ፈቃድ ከሰማይ ወረደ
እንደ ተስፋ ቃሉ ከአንቺ ተወለደ
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
ድምጹንም ሰማነው በጎለ እንስሳ
ምንኛ ድንቅ ነው የይሁዳ አንበሳ
በአንቺ ተመስርቶ ፍቅርና ሰላም
በአንድ ላይ አደሩ አንበሳና ላህም
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
ድንግል እመቤቴ የንጉሥ አገሩ
ለአዳም ተስፋው ነሽ ለኖህም ሐመሩ
የሰው ልጆች ሁሉ ተዋርደው ሲኖሩ
ከሞት ወደ ሕይወት በአንቺ ተሻገሩ
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
አዳምም ለመዳን አነባ አለቀሰ
ወደ ጥንተ ክብሩ በአንቺ ተመለሰ
በአንቺ ተፈጽሞ የአባቶች ተስፋ
ፍዳችን ተሻረ መርገማችን ጠፋ
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
ነፍስና ሥጋሽን ነስቶ ተዋሐደ
በአባቱ ፈቃድ ከሰማይ ወረደ
እንደ ተስፋ ቃሉ ከአንቺ ተወለደ
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
ድምጹንም ሰማነው በጎለ እንስሳ
ምንኛ ድንቅ ነው የይሁዳ አንበሳ
በአንቺ ተመስርቶ ፍቅርና ሰላም
በአንድ ላይ አደሩ አንበሳና ላህም
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
ድንግል እመቤቴ የንጉሥ አገሩ
ለአዳም ተስፋው ነሽ ለኖህም ሐመሩ
የሰው ልጆች ሁሉ ተዋርደው ሲኖሩ
ከሞት ወደ ሕይወት በአንቺ ተሻገሩ
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
አዳምም ለመዳን አነባ አለቀሰ
ወደ ጥንተ ክብሩ በአንቺ ተመለሰ
በአንቺ ተፈጽሞ የአባቶች ተስፋ
ፍዳችን ተሻረ መርገማችን ጠፋ
ይኸው ይኸው ተወለደ መድኅን፪
✦