አዳምን ያልተወው
✦
አዳምን ያልተወው እንደ ተሰደደ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ ፪
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተወለደ ፪
አምላካችን መድኃኒታችን
ተወለደ ለነፃነታችን ፪
ተወለደ ለነፃነታችን ፪
አዳምን ያልተወው እንደ ተጨነቀ
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ ፪
እሰይ የምሥራች ዛሬ ተጠመቀ ፪
አምላካችን መድኃኒታችን
ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪
ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪
አዳምን ሊጠራ የመጣው ሙሽራ
በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ ፪
በገሊላ መንደር ለሠርግ ተጠራ ፪
አምላካችን መድኃኒታችን
ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪
ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪
ሠርግ ቤት እንዳለ በክብር ተቀምጦ
የወይን ጠጅ ሆነ ውሀው ተለውጦ፪
የወይን ጠጅ ሆነ ውሀው ተለውጦ፪
አምላካችን መድኃኒታችን
ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪
ተጠመቀ ለነፃነታችን ፪
እጅግ ያስደንቃል የጌታችን ሥራ ፪
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ
በገሊላ መንደር ይህን ተአምር ሠራ
✦