/አዳነኝ ጌታ አዳነኝ

/አዳነኝ ጌታ አዳነኝ
ፈወሰኝ ጌታ ፈወሰኝ
እግዚአብሔር አዳነኝ ኃጢአተኛውን ወደደኝ/2
ያልፋል ያላልኩት አልፎልኝ አይቼ
በእንባ ታጠብኩኝ ከድቅድቅ ወጥቼ
እንግዲህ ላንተ ምስክር ሆኛለሁ
/ሥራህን ለዓለም ሁሌም እነግራለሁ/
ክንድህ ብርቱ ነው ደካማን ለመርዳት
ታውቅበታለህ የዛለን ማበርታት
አይኔን ከሰዎች ማራቄ ጠቅሞኛል
ደጅህ ወድቄ መኖር ተሽሎኛል
አዝ.....................
የሀዘኔን ማቅ አውልቀህ ጣልህልኝ
ሞቴን ስጠብቅ ዕድሜ ጨመርህልኝ
ከአልጋዬ ላይ አነሱኝ እጆችህ
/ተፈውሻለሁ ዛሬ በምህረት/
ቃልህ ፅኑ ነው ዳግም ይጠግናል
ጎባጣ አቅንቶ ሽባውን ተርትሯል
ሕይወቴ ባንተ ዛሬ አዲስ ሆናለች
በክብር መዝገብ በእጅህ ተፅፋለች
አዝ.......................
የሀሰትን ፍርድ ጌታ ቀለበስከው
ተጽናንቷል ባንተ ያ የተገፋ ሰው
የግፍን ጽዋ አራቅኸው ከፊቱ
/በእጁ ላይ የለም ዛሬ ሰንሰለቱ/
በሃማ መስቀል መርዶኪዮስ የለም
የናቡቴ ደም በከንቱ አልቀረም
የእውነት ዳኛ ጌታ ስትመጣ
የሀሰቱ ሰው ግፈኛው ተቀጣ
← መዝሙር