አደባባይ ቆሜ

አደባበይ ቆሜ ስምህን ከመስበክ
መጀመሪያ ልቤ ከፊትህ ይንበርከክ
ከአገልግሎት በፊት አንተን ልወቅህ
መሥዋዕት ከማቅረብ ልታዘዝልህ
አሐዱ አብ ብዬ ስምህን ብቀድስ
ለድሆች ብሰጥ ቤትህ ብገሰግስ
በመላእክት ልሳን ብዘምር በእልልታ
ምን እጠቅማሃለሁ ካልፈራሁ ጌታ
ተራራ እስካፈልስ እምነት ቢኖረኝ
ሥራ ከሌለበት ምንም አይጠቀመኝም
ልቤን ስትመረምር ከሆንኩኝ ቀላል
ክርስቲያን መባሉ ምን ይጠቅመኛል
ጨው አልጫ ቢሆን በምን ይጣፍጣል
ከውጭ ተጥሎ በእግር ይረገጣል
አንተን ለሚከተል እንዳልሆን እንቅፋት
አምልኮቴ ይሁን በፍቅር በፍርሃት
የዕውቀት ሰው መሆን አልጠቀመኝ
እኔስ መስቀልህ ነው ፍቅርህ ያሸነፈኝ
ከእምነቴ የተነሳ መታዘዝ የሆነኝ
ስምህን መፍራት ነው በእምነት የሚያኖረኝ
← መዝሙር