አድኝኝ እናቴ

አድኝኝ እናቴ ከሥጋ ፈተና
ሥጋዬ ከኃጠአት ከቶ አልራቀምና
ሸክሜ የከበደኝ ብቸኛ ሆኛለሁ
አትለይኝ ድንግል አደራ እልሻለሁ
አዝ......
የአማኑኤል እናት የተዋሕዶ አክሊል
አትጥፊ ከመሀል እንድትሆኝን ኃይል
ምንም ቢበዛብሽ የእኛ ጉስቁልና
ከእኛ ጋር ከሆንሽ አለን ቅድስና
አዝ.......
ተስፋዬ ነሽና እመኝብሻለሁ
ግራ ቀኝም አልል ምርኮኛሽ ሆኛለሁ
ስቅበዘበዝ አይቶኝ ተስፋ የሰጠኝ
እግዚአብሔር ይመስገን ኝንቺ ያስጠጋኝ
አዝ......
በሥጋ ደክሜ በነፍስ እንዳልጠፋ
እማጸንሻለሁ ድንግል የእኔ ተስፋ
የመንግሥቱ ወራሽ እንድሆን አድርጊኝ
መልኝም ሥራ መሥራት እኔን አስተምሪኝ
አዝ......
አንቺ የሌለሽበት ጉባኤው ባዶ ነው
በቁም የደረቀ ሕይወት የተለየው
በመካከል ገብተሽ ሙዪው የገአደለውን
ሠርጉ ተደግሷል ገአብኝልን ጓዳውን
← መዝሙር