አድርገህልኛልና
✦
አደርገህልኛለና በቸርነትህ፪
አመስግንሃለሁ እልል እልል /2
ለዓለም ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም ፪
ቀኑ ጨለሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
የችግር አረንቋ ፊቴ ተደኩኖ
ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈጽሞ አራቅኽልኝ የልቤን ትካዜ
አዝ ---
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ
አዝ ---
ጥቂትዋን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ
በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባሕርይህ እጹብ ለአንተ ሥራ
አዝ ---
አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይገባሀል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሠጥሃል
ድሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሠሮዬ ሞልቷል አይጎል እንደገና
አዝ ---
አመስግንሃለሁ እልል እልል /2
ለዓለም ዓለም አማኑኤል
እገዛልሃለሁ መድኃኔዓለም ፪
ቀኑ ጨለሞብኝ ዙሪያው ገደል ሆኖ
የችግር አረንቋ ፊቴ ተደኩኖ
ረዳት ያጣሁኝ በመሰለኝ ጊዜ
ፈጽሞ አራቅኽልኝ የልቤን ትካዜ
አዝ ---
አምላኬ ጉልበቴ ኃይሌ መመኪያዬ
ጠላት ማሳፈሪያ የእምነት ጋሻዬ
እንደማትተወኝ አሁን አውቄአለሁ
ካለኝ ነገር ይልቅ በአንተ ታምኛለሁ
አዝ ---
ጥቂትዋን አብዝተህ ለምትመግብ ጌታ
የምመልስልህ ባላገኝ ስጦታ
በቀንም በሌትም ሁሌ ለሚያበራ
መንክር ለባሕርይህ እጹብ ለአንተ ሥራ
አዝ ---
አምላክ ሆይ ምስጋና ለአንተ ይገባሀል
ለምስኪኗ ጎጆ በረከት ሠጥሃል
ድሃ ነኝ አልልም ሀብቴ አንተ ነህና
ማሠሮዬ ሞልቷል አይጎል እንደገና
አዝ ---
✦