አጌጥንበት ስምህን

/አጌጥንበት ስምህን
ተዋብንበት ፍቅርህን
ሞገሳችን ሆነሃል
የጽድቅ ልብሳችን አማኑኤል
ተዋህዶ የአዳምን ሥጋ
አማኑኤል ሆነ ከእኛጋ
በግርግም በቤተልሔም
ተወልዶ ሆነልን ሰላም
/አዝ/-------------
ብንጠግብ በልተን ጠጥተን
ብንገባ በሰላም ወጥተን
ልጆችን ወልደንም ብንስም
ጠርተን ነው ጌታ ያንተን ስም
/አዝ/-------------
ቢያምርብን ቢሞቀን ለብሰን
ብንረሳ ለቅሶና ሀዘን
ፍቅርህ ነው ዛሬን ያሳየን
ተመስገን እንልሃለን
/አዝ/-------------
በባዕድ ሀገር ብንኖር
ቢገጥመን መከራ ችግር
ነጩን ልብስ ለብሰን ታይተናል
መስቀሉን ከ ማህተቡ ጋር
አጌጥንበት ስምህን
ተዋብንበት ፍቅርህን
ሞገሳችን ሆነሃል
የጽድቅ ልብሳችን አማኑኤል
የዩቲዩብ ቻናላችን በዚህ ሊንክ ይጎብኙ
እስካሁን ቤተሰብ ያልሆናችሁ እየገባችሁ
← መዝሙር