አኮቴት ለ አንተ ይገባል

አኮቴት ለ አንተ ይገባል
ስብሐት ለ አንተ ይገባሀል
አምልኮ ለ አንተ ይገባል
ስግደትም ለ አንተ ይገባል
ቅድመ ዓለም የነበረ በታላቅ ሥልጣኑ
ለኩነተ ሥጋ የመጣው በፍቅሩ
ዳግምም ይህን ዓለም የሚያሳልፍ ጌታ
ኢየሱስ ክርስቶስ ኃያል የኛ አለኝታ
አዝ.
በስጋው ሲታመም ሊሞት በመስቀል
በ አብ ቀኝ የነበረ በሰማይ ሳያጎድል
ያዳምን በሕርይ ተዋሕዶ ሲያከብር
በዘህ ይገለጣል የጌታቸን ፍቅር
አዝ…..
ከቅድስት ሥላሴ የማይለይ ምክሩ
ጉድለት የለመበትም ትክክል ነው ክብሩ
የ አብ ቃል ጥበቡ አንዱ ስለሆነ
ዓለምን ፈጠረ አዳምን አዳነ
አዝ….
ሊቃነ መላእክት ኃይላቸው ነውና
ያመሰግኑታል በታላቅ ትሕትና
ዘውዳቸው ክብራቸው ስለሆነ እርሱ
ይኖራሉ ወልድን ስሙን ሲያወድሱ
← መዝሙር