አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር

አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር
ክርስቶስ ተነሣ ከህቱም መቃብር/፪ኅ/
ክርስቶስ በሞቱ ሞታችንን ሻረ
ነፍሳትን አውጥቶ ሰይጣንን አሰረ
የሲዖል እስር ቤት ባዶ ሆኖ ቀረ
በትንሣኤው ብርሃን ሰላም ተበሠረ
አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር
ክርስቶስ ተነሣ ከህቱም መቃብር
ሙስና መቃብርን በሥልጣኑ ሽሮ
የሲዖልን መዝጊያ የሞት በሩን ሰብሮ
ብርሃንን ተጎናጽፎ ሰላምን አብስሮ
ክርስቶስ ተነሥቷል አልቀረም ተቀብሮ
አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር
ክርስቶስ ተነሣ ከህቱም መቃብር
የሰንበት ጌታዋ ክርስቶሰ ሲነሣ
መርገማችን ጠፋ ቀረልን አበሳ
እርቅ ሆነ በሰማይ እርቅ ሆነ በምድር
ነፍሳት ተሻገሩ ወደ ገነት ምድር
አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር
ክርስቶስ ተነሣ ከህቱም መቃብር
ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው ጨለማ
የጥሉ ግድግዳ የሞት ጥላ ግርማ
ሸሸ ተወገደ በመስቀለ ዓላማ
የትንሣኤዉ ብስራት በዓለም ተሰማ
አልቻለም ሞት ይዞት ሊያስቀር
ክርስቶስ ተነሣ ከህቱም መቃብር
← መዝሙር