አለማመኔን እርዳው ጌታዬ

አለማመኔን እርዳው ጌታዬ
አንተ ነህና መሸሸጊያዬ
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ
ፍሬ ያላዘልኩኝ ብሆንም ጎስቋላ
ነፍሴ አብራህ ትኑር ከማደሪያህ ጥላ
አታውጣኝ ከቤትህ ባጣም ቅድስና
ይህቺን ዓመት ተወኝ ጉልበቴ እስኪጸና
አዝ
ያልጸናው ሕይወቴ ቢያስቸግርህ ላልቶ
እስኪቆም ታገሰኝ ጉልበቴ በርትቶ
እንደ ቃልህ ባልኖር ደስም ባላሰኝህ
ዛሬም ከኔ ጋር ኑር በጸናው ኪዳንህ
አዝ
ለምጼ እጅግ በዝቶ ከሰዎች ብገለል
ልትዳስሰኝ ፍጠን ምህረትን ልታደል
ደባልቀኝ ከመንጋው ከበረታው ወገን
አዘንብል ወደኔ በፈቅርህ ልሸፈን
አዝ
መዓዛዬን ለውጥ ጠረኔን ቀይረው
እንደ ናርዶስ ሽቶ የከበረ አድርገው
ቅረበኝ በፍቅርህ በደሌን ትተኸው
ሳበኝ በምሕረትህ ፊቴን ደስ አሰኘው
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ
አንተ ነህና መሸሸጊያዬ
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ
← መዝሙር