አለማመኔን እርዳው
✦
አለማመኔን እርዳው
ዘማሪት ለምለም ከበደ
===========
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ ፪
አንተ ነህና መሸሸጊያዬ
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ
አዝ--------------//
ፍሬ ያላዘልኩኝ ብሆንም ጎስቋላ
ነፍሴ አብራህ ትኑር በማደሪያ ጥላ
አታውጣኝ ከቤትህ ባጣም ቅድስና
ይቺን አመት ተወኝ ጉልበቴ እስኪ ፀና
አዝ--------------//
ያልፀናው ህይወቴ ቢያስቸግርህ ላልቶ
እስኪቆም ታገሰኝ ጉልበቴ በርትቶ
እን ደ ቃልህ ባልኖር ደስም ባላሰኝህ
ዛሬም ከእኔ ጋር ሁን በጸናው ኪዳንህ
አዝ--------------//
ለምፄ እጅግ በዝቶ ከሰዎች ብገለል
ልትዳስሰኝ ፈጠን ምህረትን ልታደል
ደባልቀኝ ከመንጋው ከበረታው ወገን
አዘንብል ወደ እኔ በፍቅርህ ልሸፈን
አዝ--------------//
መአዛዬን ለውጥ ጠረኔን ቀይረው
እንደ ናርዶስ ሽቶ የከበረ አድርገው
ቅረበኝ በፍቅርህ በደሌን ትተኸው
ሳበኝ በምህረትህ ቤቴን ደስ አሰኘው
ዘማሪት ለምለም ከበደ
===========
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ ፪
አንተ ነህና መሸሸጊያዬ
አለማመኔን እርዳው ጌታዬ
አዝ--------------//
ፍሬ ያላዘልኩኝ ብሆንም ጎስቋላ
ነፍሴ አብራህ ትኑር በማደሪያ ጥላ
አታውጣኝ ከቤትህ ባጣም ቅድስና
ይቺን አመት ተወኝ ጉልበቴ እስኪ ፀና
አዝ--------------//
ያልፀናው ህይወቴ ቢያስቸግርህ ላልቶ
እስኪቆም ታገሰኝ ጉልበቴ በርትቶ
እን ደ ቃልህ ባልኖር ደስም ባላሰኝህ
ዛሬም ከእኔ ጋር ሁን በጸናው ኪዳንህ
አዝ--------------//
ለምፄ እጅግ በዝቶ ከሰዎች ብገለል
ልትዳስሰኝ ፈጠን ምህረትን ልታደል
ደባልቀኝ ከመንጋው ከበረታው ወገን
አዘንብል ወደ እኔ በፍቅርህ ልሸፈን
አዝ--------------//
መአዛዬን ለውጥ ጠረኔን ቀይረው
እንደ ናርዶስ ሽቶ የከበረ አድርገው
ቅረበኝ በፍቅርህ በደሌን ትተኸው
ሳበኝ በምህረትህ ቤቴን ደስ አሰኘው
✦