አለና ሚካኤል
✦
አለና ሚካኤል አምላኩን ማለደው
ዘወትር ስለ እኛ መለመን ስራው ነው
ዘወትር ስለ እኛ መለመን ስራው ነው
ህጻናት በረሃብ ሲረግፉ አይቻለው
ስለዚህ አምላኬ ልማልድህ መጣው
ምድር ብረት ምጣድ ሆና ተቃጥላለች
እናት ለልጆቿ የምትሰጠው አጣች
ስለዚህ አምላኬ ልማልድህ መጣው
ምድር ብረት ምጣድ ሆና ተቃጥላለች
እናት ለልጆቿ የምትሰጠው አጣች
የሻገተ እንጀራ ፍርፋሪ ጠፋ
ምድር በውሃ ጥም በረሃብ ተቀስፋ
ስለዚህ ታረቀው ይቅር በለው አለ
ሚካኤል በሰማይ ከአምላኩ ፊት ሳለ
ምድር በውሃ ጥም በረሃብ ተቀስፋ
ስለዚህ ታረቀው ይቅር በለው አለ
ሚካኤል በሰማይ ከአምላኩ ፊት ሳለ
አይቼአለው አለ ሰባ አመት ሲቆጣ
የምህረት ፀሃይ በኢትዮጵያ ይምጣ
ሜዳው አረንጓዴ አበባ ይሞላ
ደመናው ይመለስ የምህረት ጥላ
የምህረት ፀሃይ በኢትዮጵያ ይምጣ
ሜዳው አረንጓዴ አበባ ይሞላ
ደመናው ይመለስ የምህረት ጥላ
ሚካኤል አምላኩን ማለደው በብርቱ
ዳግም እንድታበቅል አዝርዕት መሬቱ
ጠላትም እንዲያፍር ህዝቡም እንዲጽናና
እግዚአብሔር በምህረት በረድኤጥና
ዳግም እንድታበቅል አዝርዕት መሬቱ
ጠላትም እንዲያፍር ህዝቡም እንዲጽናና
እግዚአብሔር በምህረት በረድኤጥና
✦