አልተወኝም ጌታ

አልተወኝም ጌታ ለካስ ይወደኛል
ዛሬም ስበድለው ልጄ ነህ ይለኛል
ዛሬም ስበድለው ልጄ ነሽ ይለኛል
በበደል ጉራንር በሀጥያት ጫካ
ብጠፋበት እንኳ አልተወኝም ለካ
ዛሬም ልጄ ብሎ ዳግም ይጠራኛል
ለካስ አልጠላኝም ጌታ ይወደኛል
አዝ ...
ለስልጣን ለክብሬ ብዬ ስክደው
ለገንዘብ አድልቼ እኔ ብረሳው
ለእኔ ያለው ፍቅር አልቀነሰብኝም
ዛሬም ይወደኛል ጌታ አልጠላኝም
አዝ ...
ታዲያ ለዚህ ፍቅሩ ለሌለው ወሰን
ከጭንጫ መቃብር ላወጣኝ እኔን
በሕይወቴ ሁሉ ፍፁም ለመራኝ
ክብርና ምስጋናን አቀርባለሁኝ
← መዝሙር