አማልጅ ነው
✦
አማላጅ ነው ሚካኤል
በፍጡራን እና ፈጣሪ መካከል
ስልጣን የተሰጠው ሰውን ለማገልገል
ተራዳኢው መልአክ ጠባቂ የእስራኤል
የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል
ስልጣን የተሰጠው ሰውን ለማገልገል
ተራዳኢው መልአክ ጠባቂ የእስራኤል
የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል
አማላጅ ነው ሚካኤል፪ የአምላክ ባለሟል
የነሙሴ የሕዝበ ፳ኤል ፪
የነሙሴ የሕዝበ ፳ኤል ፪
አምላከ እስራኤል ታማኝ ጌታችን
ለእስራኤል ለሙሴ የሆንከው መድኅን
ፈርኦን እንደገና በትእቢት ቢገን
ለእስራኤል መሪ መረጥከው ሙሴን
አዝ
ፈርኦን በእሥራኤል ላይ በትዕቢት ተነስቶ
ሲከታተላቸው ጦሩን አስከትቶ
ይመራቸው ነበር ሚካኤል በፋና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
አዝ
ሙሴ እንደታዘዘው አነሳ በትሩን
እጆቹን ዘረጋ ገሰጸው ባሕሩን
እንደ ግንብ ቆመ ባሕረ ኤርትራ
በደረቅ አለፉ እስራኤል በተራ
አዝ
ከባሕር ያወጣኸው ጸጋ ዘአብን
ከአረመኔው ንጉሥ እግዚእ ኃረያን
ከልለህ የጠበቅኽ በታላቅ ታምራት
እኛንም ጠብቀን ከበደል ከኃጢያት
አዝ
በአፎምያ ላይ ሲፎክር ጠላት
ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላእክት
እኛንም ጠብቀን ከክፉ መቅሰፍት
ፈጥነህ ድረስልን ሁነን እረዳት
አዝ
መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን
እንማልድሃለን እንድትጠብቀን
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ
ዋስ ጠበቃ ሁነን ሚካኤል አደራ
አዝ
ለእስራኤል ለሙሴ የሆንከው መድኅን
ፈርኦን እንደገና በትእቢት ቢገን
ለእስራኤል መሪ መረጥከው ሙሴን
አዝ
ፈርኦን በእሥራኤል ላይ በትዕቢት ተነስቶ
ሲከታተላቸው ጦሩን አስከትቶ
ይመራቸው ነበር ሚካኤል በፋና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
አዝ
ሙሴ እንደታዘዘው አነሳ በትሩን
እጆቹን ዘረጋ ገሰጸው ባሕሩን
እንደ ግንብ ቆመ ባሕረ ኤርትራ
በደረቅ አለፉ እስራኤል በተራ
አዝ
ከባሕር ያወጣኸው ጸጋ ዘአብን
ከአረመኔው ንጉሥ እግዚእ ኃረያን
ከልለህ የጠበቅኽ በታላቅ ታምራት
እኛንም ጠብቀን ከበደል ከኃጢያት
አዝ
በአፎምያ ላይ ሲፎክር ጠላት
ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላእክት
እኛንም ጠብቀን ከክፉ መቅሰፍት
ፈጥነህ ድረስልን ሁነን እረዳት
አዝ
መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን
እንማልድሃለን እንድትጠብቀን
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ
ዋስ ጠበቃ ሁነን ሚካኤል አደራ
አዝ
✦