አማናዊት እናት

አማናዊት እናት እነኋት ማርያም
ለቅዱስ ዮሐንስ ተሰጠች ለዓለም
ድኅነት የምታሰጥ የዘለዓለም ህይወት
የኛ ተስፋችን ናት ኪዳነ ምሕረት
ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ
ተዋሐደ አምላክ
አልተለየችም በማዳኑ ስራ እናታችን
ጽዮን ማርያም መጠጊያ ጥላችን
አማናዊት እናት እነኋት ማርያም
ለቅዱስ ዮሐንስ ተሰጠች ለዓለም
ወልዳ አሳደገች አዝላ ተሰደደች
የሁላችን እናት ድንግል ተንከራታለች
ከእግረ መስቀሉ ከዙፋኑ በቀኝ ቆማለች
ትላንት ዛሬም ነገም ማርልኝ እያለች
አማናዊት እናት እነኋት ማርያም
ለቅዱስ ዮሐንስ ተሰጠች ለዓለም
← መዝሙር