አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ

አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ
የግብፅ ከተማ ደምቃ ስትታየኝ
ተስሎንቄ አድጋ ለዓይኔ ስትስብኝ
ኤልሻዳይ ኢየሱስ ልቤን መልስልኝ
አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ
መታመን በሰው ላይ ምንም አይጠቅምም
መከታነት በሰው ለእኔ አይሆንም
አትተወኝ አንተ አምላክ ዘለዓለም
አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ
የሚያጽናናኝ የለም እኔ እንዲህ ስከፋ
ህምልምም ሆነብኛል የሰው ሁሉ ተስፋ
ቃልህን የሚታጥፈው አንተ ከእኔ አትጥፋ
አማኑኤል ሆይ መድኃኒቴ ሆይ
አትተወኝ አንተ ሞትን እንዳላይ
← መዝሙር