አመ አመ ሰበክሙ

አመ አመ ሰበክሙ
ቅዱሳን ሐዋርያት
ቅዱሳን ሐዋርያት ......... ሐዋርያት
የዓለም ብርሃናት ........... ሐዋርያት
መጀመሪያው ጴጥሮስ ....... ሐዋርያት
ኋለኛው ጳውሎስ ............... ሐዋርያት
አዝ.....
ብርሃናተ ዓለም ............. ሐዋርያት
ጴጥሮስ ወጳውሎስ ...... ሐዋርያት
በእውነት ተሰየፉ .......... ሐዋርያት
ስለ ክርስቶስ ................. ሐዋርያት
አዝ.....
ሐዋርያት ዘርተው ........ ሐዋርያት
ሲለቅሙ በሻማ ............ ሐዋርያት
ሰዎች አትለዩ ............... ሐዋርያት
ከወንጌል ዓውድማ ....... ሐዋርያት
አዝ.....
የዘለዓለም ሕይወት ...... ሐዋርያት
ማግኘት ያማራችሁ ...... ሐዋርያት
የሐዋርያት ሥራ .......... ሐዋርያት
ይሁን ዓላማችሁ .......... ሐዋርያት
አዝ.....
ውኆች ቀለም ሆነው ..... ሐዋርያት
እንጨቶች ብዕር ............ ሐዋርያት
ቢጽፉት አያልቅም ......... ሐዋርያት
የሐዋርያት ግብር.............ሐዋርያት
← መዝሙር