አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ

አምላክ ሆይ ወደኛ ባትመጣ ለብሰህ የማርያምን ሥጋ
ባክኖ የኖረው የአዳ ዘር ውጤቱ ነበር የሚያሰጋ
በዚያች ዓመት በዚያች ወር በዚያች ቀን
ድህነትን ለሰው ልጅ ስትሰጥ
ምን ይበዛ ነበር ትሕትናህ፣ ትዕግሥትህ የማይለወጥ
የሾህ አክል ደፍተህ በራስህ ጎንህን ሲወጉህ በጦር
አንተ ግን ለነረሱ ካባትህ ምሕረትን ስትጸልይ ነበር
ግን መቼ አወቁት እነርሱ በኃጢአት ደንድኖ ልባቸው
መድኃኒታቸውን ገረፉህ ሰቀሉህ አንተም ሞትክላቸው
ዳግም ስትመጣ ለፍርድ ከዓለም ፍጻሜ በኋላ
እንዴት ዕድለኞች ናቸው ካንተ የሚያኙት ተድላ
በዚያች በደብረ ዘይት ቦታ ደስታን ለቅሶ ሲፈልቅ
ከቶ ወዴት ይሆን ዕድሌ ያንጊዜ የኔ አወዳደቅ
የፀፀጽ ሮሮ በፊትህ እንዳያቃጥለኝ እኔን
እርዳኝ ፈጣሪዬ ካሁኑ አንጻው የዛገው ልቤን
ዘማሪ የሺህ እመቤት
← መዝሙር