አምላክ ሆይ የኢትዮጵያን

እግዚኦ ሰላመከ ሃባ ለሃገር ጽድቀከኒ ለቤተክርስቲያን አግርር ጸራ ታህተ ለአገሪትነ ኢትዮጵያ
✞አምላክ ሆይ የኢትዮጵያን✞
አምላክ ሆይ የኢትዮጵያን ልመናዋን ስማ
እጆቿን ዘርግታ ስትማጸን ቆማ
በደም ስላስጌጧት በደም ስላጸኗት
ስለ ቅዱሳኗ በረከትን ስጣት
ረሃብ ጉስቁልና ፊቷን አጥቁሮታል
የልጇቿ እንግልት እረፍት ነስቷታል
ስለ ድንግል ብለህ ስለ አዛኝቱ
የአስራት ልጇቿ መልካም ይመልከቱ
እኔ እበለጥ እኔ እሻል እየተባባሉ
የአንድ አባት መሪዎች ጦር ይማዘዛሉ
ዙፋንህ በሆነች በታቦተ ጽዮን
ከእግሮቿ ስር ይጣል መለያየት ተንኮል
በህዝቦቿ ልብ ውስጥ ጠላት እሾህ ዘርቷል
ወንድም ወንድሙ ላይ እጆቹን አንስቷል
በግሸን ተራራ ስላለው መስቀልህ
ከጥፋት ታደጋት ጥልን አስወግደህ
በዙሪያዋ ከበው የሚጠሏት ሁሉ
መውደቋን መጥፋቷን ይጠባበቃሉ
ስለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ስለ ጠባቂዋ
የተፈራ ይሁን ዙሪያ ዳር ድንበሯ
መሃረነ አብ ሃሌ ሉያ
ተሰሃለነ ወልድ ሃሌ ሉያ
መንፈስቅዱስ መሐሪ ተዘከረነ በሣህልከ
መዝሙር
የቦሌ ኆኅተ ብርሃን
ቅድስት ማርያም ሰ/ት/ቤት
← መዝሙር