አምላክ ዘበአማን
✦
አምላክ ዘበአማን ኢየሱስ ክርስቶስ፪
እውነተኛ ፈራጅ መንግሥቱን የሚያወርስ፪
ለድንግል ማርያም ልጅ ለዘለዓለም ጌታ
ምስጋናን እናቅርብ ከጧት እስከ ማታ
እውነተኛ ፈራጅ መንግሥቱን የሚያወርስ፪
ለድንግል ማርያም ልጅ ለዘለዓለም ጌታ
ምስጋናን እናቅርብ ከጧት እስከ ማታ
መስቀል ላይ ተሰቅሎ ዓለምን አድኗል
ዲያብሎስን አሥሮ መርገምን አጥፍቷል
ኢየሱስ የሚለው መድኃኒት፪ ነው ስሙ
ከክፉ ያድናል ልዩ ነው፪ ጣዕሙ
ዲያብሎስን አሥሮ መርገምን አጥፍቷል
ኢየሱስ የሚለው መድኃኒት፪ ነው ስሙ
ከክፉ ያድናል ልዩ ነው፪ ጣዕሙ
አዝ
ቅዱሱ ሥጋውን የከበረ ደሙን
ብሉ ጠጡ ያለ የሰው ልጅ እንዲድን
ኢየሱስ ክርስቶስ የአማልክት፪ አምላክ የነገሥታት ንጉሥ
የጌቶችም ጌታ ዘለዓለም፪ ይወደስ
ብሉ ጠጡ ያለ የሰው ልጅ እንዲድን
ኢየሱስ ክርስቶስ የአማልክት፪ አምላክ የነገሥታት ንጉሥ
የጌቶችም ጌታ ዘለዓለም፪ ይወደስ
አዝ
በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከድንግል ያለ አባት
በተዋሕዶ ከብሮ ተወልዷል በእምነት
ጥበብም በእጁ ነው ፈጣሬ፪ ዓለማት
ኢየሱስ ክርስቶስ ርኅሩኅ፪ ነው ቸር አባት
አዝ
በተዋሕዶ ከብሮ ተወልዷል በእምነት
ጥበብም በእጁ ነው ፈጣሬ፪ ዓለማት
ኢየሱስ ክርስቶስ ርኅሩኅ፪ ነው ቸር አባት
አዝ
አማላጅ አይደለም ነቢይም አይደለም ይነገር እውነቱ
ተማላጅ ነው እንጂ የነቢያት አምላክ ኃያል ጌትነቱ
ለፍጡራን አምላክ ለሚምር፪ ለሚያድን
ለሚያድል በረከት ሰላምን ሰላምና ፍቅርን
ለኢየሱስ ክርስቶስ እንስገድ የአምልኮ ስግደትን
ተማላጅ ነው እንጂ የነቢያት አምላክ ኃያል ጌትነቱ
ለፍጡራን አምላክ ለሚምር፪ ለሚያድን
ለሚያድል በረከት ሰላምን ሰላምና ፍቅርን
ለኢየሱስ ክርስቶስ እንስገድ የአምልኮ ስግደትን
✦